የተባባሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 11.05.2022
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የተባባሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ

ኢሰመኮ ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና የዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበዉ የ10 ወር ዘገባዉ እንዳለዉ በየጊዜዉ በሚያገረሹ ግጭቶች ምክንያት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየጨመረ፣ ተጠያቂነትና የሕግ የበላይነት እየላላ ነዉ።

«ምክር ቤቱ አስፈፃሚዉን አካል መከታተል አለበት» አሰመኮ

 የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሐገሪቱ ዉስጥ እየከፋ የመጣዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመከላከል እንዲጥርና መንግሥትን እንዲቆጣጠር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ።ኢሰመኮ ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና የዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበዉ የ10 ወር  ዘገባዉ እንዳለዉ በየጊዜዉ በሚያገረሹ ግጭቶች ምክንያት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየጨመረ፣ ተጠያቂነትና የሕግ የበላይነት እየላላ ነዉ። ኮሚሽኑ አክሎ እንዳለዉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ከፍርድ ቤት ዉሳኔ ውጪ የሚፈፀምሙት ግድያ፣ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ፣ የዘፈቀደ እሥር እና የፍርድ ቤት ትእዛዝ አለመከበር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።ምክር ቤቱ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብሏልም-ኮሚሽኑ።

ሰለሞን ሙጪ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች