የተባበሩት መንግስታት ፀረ የሰው ልጆች ቁም ስቅል ዕንቅስቃሴ | የጋዜጦች አምድ | DW | 26.06.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

የተባበሩት መንግስታት ፀረ የሰው ልጆች ቁም ስቅል ዕንቅስቃሴ

የሰው ልጆችን በቁም ማሰቃየት ሰብዓዊ መብትን መጣስ ነው።

ድርጊቱን በሚፃረረው ዓለም ዓቀፍ ስምምነት ተግባሩ ህገ ወጥ መሆኑ ተደንግጎዋል። በዓለማችን ላይ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ልዩ ልዩ የቁም ስቅሎችን ለማስቆም በየጊዜው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ህጎች ቢወጡም ፣ ውሳኔዎች ቢተላለፉም አሁንም በብዙ ሀገራት ይህን መሰሉ ድርጊት አልቆመም ። በዚህም የተነሳ ፀረ የሰው ልጆች ስቃይ ዕንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። ትግሉን ውጤታማ ለማድረግም ባለው ዓለም ዓቀፍ ውል ላይ ተጨማሪ ድጋፍ የሚሰጥ ስምምነት በቅርቡ ወጥቶዋል ። ባለፈው ሀመስ የወጣው ለተባበሩት መንግስታት ፀረ የሰው ልጆች ቁም ስቅል ውል ድጋፍ ሰጭ የሆነው የተጨማሪው ስምምነት ዋነኛ ዓላማ የሰው ልጆችን ቁም ስቅል መከላከል ነው።ስምምነቱ አገራት ድርጊቱን ለመከላከል በብሄራዊ ደረጃ አዲስ የመቆጣጠሪያ ስልት ያካተተ አሰራር እንዲቀይሱ ያስገድዳል ።በብሄራዊ ደረጃ የሚቋቋመው ድርጊቱን የሚከታተለው አካልም በተባበሩት መንግስታት ኮሚቴዎች ቁጥጥር ይደረግበታል ። ከከዚህ ቀደሙ ልምድ በመነሳትም አሰራሩ ለየት ይላል ። ለምሳሌ በፖሊስ ጣቢያዎች ወይም በወህኒ ቤቶች ላይ የሚደረጉ ክትትሎች አቤቱታ እስኪመጣ መጠበቅ የለባቸውም መስሪያቤቶቹ አስቀድሞ ስለጉብኝቱ ሳይነገራቸው ድንገተኛና ያልታሰበ ቁጥጥር እንዲደረግ ነው የታሰበው ።ይኽው በኮስታሪካ አነሳሽነት እአአ በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያዎቹ የተነቃቃው የተጨማሪው ስምምነት ሀሳብ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቴክኒክና የውሳኔ ሰጭ ኮሚቴዎች ዘንድ ረዥም ጊዜ የወሰደ ክርክር ተካሂዶበታል ። በተለይ ብዙ ያነጋገረው የሰዎችን የቁም ስቅል መከላከያው ዘዴ በብሄራዊው ውይስ በዓለም ዓቀፉ ተቆጣጣሪ አካል ስር ይሁን የሚለው ጥያቄ ብዙ አነጋግሮዋል።ሆኖም በመጨረሻ መግባባት ላይ ተደርሶዋል። የጀርመን የሰብዓዊ መብት ተቅዋም ሀላፊ ሀይነር ቢሊፌልት
ድምፅ
“በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም ጥሩ መግባባት ላይ ነው የተደረሰው። ማለትም ከሁለቱም አካላት ምርጥ ምርጡን ያዋሀደ ነበር ። በአንድ በኩል ዓለም ዓቀፍ ቁጥጥር ይኖራል። በብሄራዊ ደረጃም ቢሆን ቁጥጥር ይደጋል።”
በርሊን የሚገኘው የጀርመን የሰብዓዊ መብት ተቅዋም ሀላፊ ቢሊፊልት ተጨማሪውን ስምምነት የሰውልጆችን የቁም ስቃይ እንዲሁም ጭካኔ የተሞላበትን ሰብዓዊ አያያዝ ለማስቆም በዓለም ዓቀፉ ጥረት ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሲሉ አወድሰውታል ። ኮስታሪካ ፣ ቦሊቪያ ሆንዱራስ ፣ ዴንማርክ ና እንግሊዝን ጨምሮ ሀያ አገራት ስምምነቱን መቀበላቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ በፊርማቸው አፅድቀዋል። ጀርመን ከስምምነቱን ፈራሚ የመጀመሪያዎቹ አገራት ውስጥ አልተካተተችም ።ቢሊፊልት አስተያየታቸውን እንደሰጡት ሀገራቸው በቅርቡ ስምምነቱን ትቀበላለች ብለው ይገምታሉ።
ድምፅ
“ጀርመን አሁን ከመጀመሪያዎቹ የስምምነቱ ፈራሚ ሀያ አገራት ውስጥ መሆን አልቻለችም።ሆኖም በጥቂት ወራት ውስጥ ወደስምምነቱ ትመጣለች የሚል ግምት አለን”
ቢሊፊልት ጀርመን ስምምነቱን ለመፈረም ቀዳሚ ያልሆነችበትን ምክንያትም ከተጨባጭ ሁኔታ ተነስተው እንደተናገሩት ችግሩ የጀርመን ምክርቤት ስለጉዳዩ የፖለቲካ ፈቃደኝነት ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን የሀገሪቱ ፌደራላዊ አወቃቀር የተባለውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የማስቻሉ አጣያያቂነት ነው። ለምሳሌ እያንዳንዱ የጀርመን ፖሊስ ጣቢያ ተጠሪነቱ ለየፌደራል መንግስቱ ነው ብለዋል።ከጀርመን አጠቃላይ ስፋት አንፃር ቁጥጥር የሚያስፈልጋቸው ስፍራዎች ብዙ ናቸው።ሰዎች የሚያዙባቸው ዕስርቤቶች ፖሊስ ጣቢያዎች በተጨማሪም የስነ ልቦና ችግር ያለባቸው በሽተኞች ክትትል የሚደረግባቸው ሀኪም ቤቶች ላይ የቁጥጥር ስልት ለመዘርጋት ብዙ ወጪ ይጠይቃል። እንደ ጀርመን ሁሉ በየሀገሩ በሚነሱ ልዩ ልዩ ሰበቦች የተነሳ ቢሊፊልት እንዳሉት የሰውልጆችን የቁም ስቃይ ለማስቆም የሚደረገው ጥረት ባለፉት ዓመታት ወደ ህዋላ ነው የሄደው
ድምፅ
“ፀረ የሰው ልጆች የቁም ስቃይ ትግል ባለፉት ዓመታት የህዋሊት ነበር የሚራመደው።ይህም
በተለይም መስከረም አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ሽብርተኖች በኒውዮርክ ካደረሱት ጥቃት በህዋላ አጠቃላዩ ሁኔታ ከመቀያየሩ ጋር ይያያዛል።ከጥቃቱ በህዋላ ይበልጡን የተንቀሳቀሰው የፀረ ሽብርተኝነት ፖለቲካ ነበር።ይህም አሁንም በተጨማሪው ስምምነት የሰብዓዊ መብትን ጉዳይ ማካተት የሚያስችል ነው። የሰው ልጆችን የቁም ስቃይ የመከላከሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ። ይህን ተግባራዊ ለማድረግም አመቺ ሁኔታዎች አሉ።”