የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 75ኛ ዓመት | ዓለም | DW | 29.06.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 75ኛ ዓመት

ዓለም እጅግ የከፋ የጤና፣ የኤኮኖሚ እና የማኅበራዊ ሕይወት ቀውስ በገጠመው በዚህ ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 75ኛ ዓመቱን ዘክሯል። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሐሙስ የተባበሩት መንግሥታትን 75ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ዓለም አቀፍ ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዓለም እጅግ የከፋ የጤና፣ የኤኮኖሚ እና የማኅበራዊ ሕይወት ቀውስ በገጠመው በዚህ ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 75ኛ አመቱን ዘክሯል። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሐሙስ የተባበሩት መንግሥታትን 75ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ዓለም አቀፍ ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። ይሁንና እንደ አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አይነት መሪዎች የሚከተሉት አቋም ድርጅቱ ለቆመት መርኅ ፈተና ሆኗል።

ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር የተፈረመበት 75ኛ ዓመት ሲታሰብ እንዳሉት አገሮች የሚተባበሩበት መንገድ እንደገና ሊፈተሽ ይገባል። የድርጅቱ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ አባላት የሆኑት አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ እና ብሪታኒያ በመጪው መስከረም ተገናኝተው ልዩነቶቻቸውን ያስታርቃሉ የሚል ተስፋቸውንም ገልጸዋል። የድርጅቱ ቻርተር የተፈረመበት 75ኛ አመት የተዘከረው ባለፈው አርብ ሰኔ 19 ቀን 2012 ነበር።

የድርጅቱ ቻርተር በአባል አገራት ጸድቆ የተፈረመው ሰኔ 19 ቀን 1937 ዓ.ም  በአሜሪካዋ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማ ነበር።  

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ