የተባበሩት መንግሥታት የንግድና የልማት ጉባኤ ዘገባ | ኤኮኖሚ | DW | 25.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የተባበሩት መንግሥታት የንግድና የልማት ጉባኤ ዘገባ

በዓለም ዙሪያ የውጭ ባለሃብቶች ውረታ እጎአ በ2013 አፍሪቃን ጨምሮ አድጓል ። ግን በአፍሪቃ የእድገቱ መጠን ከሌላው የዓለም ክፍል ጋር ሲነፃጸር ዝቅ ያለ ነው ። የተባበሩት መንግሥታት የንግድና የልማት ጉባኤ በምህፃሩ UNCTAD ትናንት ባወጣው ዘገባ መሠረት በዓለም ዙሪያ የመሰረተ ልማት ግንባታና የኩባንያዎች እንቅስቃሴ በ9 በመቶ አድጓል ።

China Afrika Wirtschaft

በመላው አፍሪቃ ደግሞ የአራት በመቶ እድገት አስመዝግቧል በአንዳንድ አካባቢዎችና በአፍሪቃ ሃገራት የእድገቱ መጠን ከቦታ ቦታ ልዩነት ይታይበታል ፍሬድሪከ ሙለር ያነጋገረቻቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የግል ንግድ ድርጅት መሪ ወይዘሮ ሙሉ ሰሎሞን ወደ ሃገራቸው ኢትዮጵያ የሚገቡ ዓለም ዓቀፍ ባለወረቶች ስብጥር እየተለወጠ በመሄድ ላይ መሆኑን ታዝበዋል ይህም አስደሳች ሆኖ አግኝተውታል።

« መጀመሪያ ላይ የሚመጡት ቻይናውያን ቱርኮችና ህንዶች ነበሩ አሁን ግን ያለውን ሰፊ የስራና የገበያ እድል በመረዳት የምዕራባውያን ሃገራት ባለሃብቶች እየገቡ ነው »

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወይዘሮ ሙሉ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የኢትዮጵያ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ነበሩ በዚህ ሃላፊነታቸውም የውጭ ባለ ሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው እንዲሰሩ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ እና ሥራቸውን የሚገድቡ ቢሮክራሲያዊ ደንቦችም እንዲቃለልላቸው ይታገሉ ነበር ።በወይዘሮ ሙሉ አስተያየት የውጭ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ መወረታቸው ሃገሪቱን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተጠቃሚ እያደረገ ነው

Logo UNCTAD

« ከፍተኛ እድገት ካስመዘገቡ ሃገራት ጋር አብረን ስንሰራ ለኛ ብዙ ጥቅም አለው ከነርሱ ትምህርት እንቀስማለን የስራ እድል መፍጠራቸው አንዱ ጥቅም ነው ሌላው ጥቅም ደግሞ የምርት ጥራትም ከፍ ማለት ነው የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪን ብንወስድ እንኳን አንድ ኩባንያ 10 ሺህ ሠራተኞችን ቀጥሮ ያሰራል ።ሌላው ደግሞ ወደ ስምንት ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል ።ይህ ለኛ ትልቅ የስራ ገበያ እድል ነው »

ኢትዮጵያ በጎርጎሮሳውያኑ 2013 ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ጋር ሲነፃጸር 2012 የበለጠ ቀጥተኛ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት በብዛት የተካሄደባት ሃገር ናት የተባበሩት መንግሥታት የንግድና የልማት ጉባኤ በምህፃሩ UNCTAD እንደሚለው 2013 በምሥራቅ አፍሪቃ የዓለም ዓቀፍ ባለ ሃብቶች ውረታ 15 በመቶ ከፍ ብሏል ከነዚህ ውረታዎች አብዛኛዎቹ በኢትዮጵያና በኬንያ ነው የተካሄዱት። 2013 በአፍሪቃ ከፍተኛው የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት የተመዘገበው ግን ደቡባዊ አፍሪቃ ውስጥ ነው 2012 ጋር ሲነፃፀር በደቡባዊ

Öl Raffinerie in Juba, Sudan

አፍሪቃ የውጭ ባለሃብቶች ውረታ በእጥፍ ጨምሯል ባለሃብቶች በይበልጥ የተሰማሩትም በደቡብ አፍሪቃ በዚምባብዌ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ነበር በተቀሩት የአፍሪቃ ሃገራት አነስተኛ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ነው የተመዘገበው ለዚህም UNCTAD ፖለቲካዊ አለመረጋጋትንና በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ ቀውሶችን በምክንያትነት አስቀምጧል

በዚህ ረገድ ድርጅቱ የሰሜን አፍሪቃው ቀውስ በምዕራብ አፍሪቃዋ በናይጀሪያ የተፈጠረው አስተማማኝ ያልሆነ ሁኔታ እንዲሁም የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክን የርስ በርስ ጦርነት ጠቅሷል የጀርመኑ የዓለም ዓቀፍና አካባቢያዊ ጥናቶች ተቋም በምህፃሩ GIGA ባልደረባ ሮቤርት ካፕል የውጭ ባለወረቶችን የሚገፉና የሚስቡ ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ ይገልፃሉ።

«ባለወረቶች የርስ በርስ ጦርነት ወይም ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ወዳለበት ሃገር አይመጡም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ግን ይሄዳሉ ባለፉት ዓመታት አንዳንድ

ሃገራት በጣም የተሳኩ ተግባራት አከናውነዋል በምሥራቅ አፍሪቃ በአንዳንድ የታላላቅ ኃይቆች ሃገራት ለምሳሌ በሩዋንዳ በኡጋንዳ ብዙ ተከናውኗል ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት ባሉበት በኢትዮጵያና በአንጎላ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈጠር በማድረግ ባለወረቶችን ለማማለልና በኢንዱስትሪው ልማት እንዲሰለፉ ለማድረግ አብቅተዋል። »

አፍሪቃ ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ላቅ ያለ ትርጉም እየተሰጣቸው ነው በሌላ በኩል በጥሬ ሃብት ዘርፍ ያለው እንቅስቃሴ ግን ያን ያህል አይደለም ከዛሬ አስር ዓመት በፊት ግን በአፍሪቃ በዘርፉ የተካሄደው የመዋእለ ንዋይ ፍሰት ከአጠቃላዩ ውረታ ከግማሽ በላይ ነበር በአሁኑ UNCTAD ዘገባ እንደተመለከተው ግን አንድ አስረኛውን ድርሻ ብቻ ነው የሚይዘው

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic