የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የደም ልገሳ | ኢትዮጵያ | DW | 06.11.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የደም ልገሳ

የርሀብ አድማ ለማድረግ መከልከላቸውን የገለፁት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ዛሬ የደም ልገሳ አደረጉ። 71 የሚሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአዲስ አበባ መስተዳደር የረሀብ አድማውን ሊያደርጉ ያሰቡበትን ስፍራ ጠቅሰው ላቀረቡት ምላሽ አለማግኘታቸውን በትናንትናው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:26

«የረሀብ አድማው አልቀረም»

ብዙዎች ለሕይወት ጥፋት እና ስቃይ ብሎም ለመፈናቀል በተጋለጡበት በዚህ ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የርሀብ አድማም ሆነ ሌላው ርምጃ ሊያስከትል የሚችለው ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ጥያቄ እየቀረበበት ነው። ፖለቲከኞቹ በበኩላቸው በሰላማዊ የትግል ስልት ራስን የማስራብ ውሳኔ የመጨረሻው እና ትኩረትን የሚስብ ርምጃ መሆኑን ያስገነዝባሉ። የደም ልገሳ በሚደረግበት ስፍራ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች