የተቃዉሞ ሠልፍ በለንደን | አፍሪቃ | DW | 13.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የተቃዉሞ ሠልፍ በለንደን

ዛሬ ለንደን ብሪታንያ ምክር ቤት ፊትለፊት የተሠለፉት የኦሮሞ ተወላጆች እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነዉ።የብሪታንያ መንግሥት ሠልፈኞቹ «ዜጎቹን ይበድላል» ላሉት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሠጠዉን ድጋፍ እንዲያቆም ሠልፈኞቹ ጠይቀዋል

ብሪታንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የኦሮሞ ተወላጆች የኢትዮጵያ መንግሥት በሐገሪቱ ሕዝብ በተለይም በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይፈፅመዋል ያሉት የሠብአዊ መብት ረገጣ እንዲያቆም በሠላማዊ ሠልፍ ጠየቁ።ዛሬ ለንደን ብሪታንያ ምክር ቤት ፊትለፊት የተሠለፉት የኦሮሞ ተወላጆች እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነዉ።የብሪታንያ መንግሥት ሠልፈኞቹ «ዜጎቹን ይበድላል» ላሉት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሠጠዉን ድጋፍ እንዲያቆም ሠልፈኞቹ ጠይቀዋል።ጥያቄያቸዉን ለብሪታያ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በደብዳቤ ማመልከታቸዉንም አስታዉቀዋል።የለንደንዋ ወኪላችን ሐና ደምሴ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።

ሐና ደምሴ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic