የተሰዳጆች መበራከትና የአፍሪቃ መሪዎች ቸልታ | አፍሪቃ | DW | 07.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የተሰዳጆች መበራከትና የአፍሪቃ መሪዎች ቸልታ

ወደ አዉሮጳ ለመግባት ተመኝተዉ የተወለዱበትና የኖሩበትን አካባቢ እየተዉ የሚሰደዱ አፍሪቃዉያን ቁጥር ከዕለት ወደዕለት እየጨመረ መሄዱ እየታየ ነዉ። ተሰዳጆቹ ከየሀገራቸዉ የሚወጡበት የተለያየ ቢሆንም ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸዉ በራሳቸዉ ሀገር ብሩህ ተስፋ ማጣታቸዉ እንደሆነ ይታመናል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 27:35
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
27:35 ደቂቃ

የአፍሪቃ ስደተኞች

በአንድ ወገን የተሰዳጆቹ ቁጥር መበራከት በሌላ በኩል ደግሞ ወደአዉሮጳ ለመድረስ የሜድትራኒያንን ባህርን ለማቋረጥ ሲሞክሩ ለአደጋ መጋለጣቸዉ የአዉሮጳ ሃገራት መሪዎች አሳስቧል አደናግጧል። እነሱን ከመስጠም ለማዳንም ሆነ ሳይነሱ በደረሱበት መሸጋገሪያ ሀገር ለማስቀረት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የአብዛኞቹ ስደተኞች መፍለቂያ የሆነችዉ አፍሪቃ መሪዎች በተቃራኒዉ ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት የሰጡት አይመስልም። የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት እንወያይ መሰናዶ የአፍሪቃዉያን ስደተኞች መበራከትና የአፍሪቃ ኅብረትን ቸልታ ይመለከታል። ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic