የተሰናባቹ ዓመት ቅኝት | ጤና እና አካባቢ | DW | 29.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የተሰናባቹ ዓመት ቅኝት

ከነገ በስተያ አሮጌ የምንለዉ ተሰናባቹ የአዉሮጳዉያን 2009ዓ,ም ገና ሳይመጣም ሲናፈቅ ተከርሟል።

default

...ጭስ የተረፈዉ ጉባኤ...

ከምንም በላይ በአንድ ዓቢይ ጉዳይ የአየር ጠባይ ለዉጥ መግታት የሚያስችል፤ የኪዮቶዉን ዉል የሚተካ መንግስታት በጋራ መክረዉ ዘክረዉ የሚያመጡትን ስምምነት ያስገኛል በተባለዉ ጉባኤ አማካኝነት። የኮፐንሃገኑ የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ ግን የታለመለትን ግን ሳይመታ፤ እንደዉ ተስፋ የማይቆርጡትን ጉዳዩን በኃላፊነት የሚያራምዱ ወገኖችን በጎ ምኞት እንደያዘ በዚህ ዓመት የታሰበዉ ሳይገንበት ታለፈ። ለነገሩ ጉባኤ እንደዉ ሁሉም በዙሮ ተባዝቶ ዉጤቱም ዜሮ ነዉ የማይባልበት ነገር መፍጠሩ አልቀረም። እስከዛሬ የአካባቢ ተፈጥሮ መጎዳት፤ ብሎም የአየር ጠባይ ለዉጥ ክስተት ተጋርዶባቸዉ ለከረመ የዓለም የፖለቲካ ተዋናዮች ብርሃን አብርቶላቸዋል።

ከቀናንና መጪዉ 2010ዓ,ም ገደኛ ከሆነ የአየር ጠባይ ለዉጥና ተያያዥ መዘዞቹን ለመግታት የሚያስችል ስምምነት ያመጣ ይሆናል። 2009 ቢለፋም በዚህ በኩልስ አልተሳካለትም። ሰርቶ መሰናበት ያለነዉና ከነገ በስተያ እንሸኘዋለን። ዳግም አይመለስም፤ ታህሳስ 2009 በኮፐንሃገንም እያልን ተስፋ ማድረጋችን ይበቃል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ