የተራዘመዉ «ለወገኔ እሮጣለሁ» ሩጫ በኦሮሚያ | ኢትዮጵያ | DW | 16.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የተራዘመዉ «ለወገኔ እሮጣለሁ» ሩጫ በኦሮሚያ

ከኢትዮጵያ ሶማሊ እና ከኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች ለተፈናቀሉ ሰዎች መርጃ የሚዉል ገንዘብ ለመሰብሰብ የአሮሚያ አትሌቲክስ ማሕበር «ለወገኔ እሮጣለሁ» በሚል መሪ ቃል ታላቅ የሩጫ ዉድድር እንደሚያኪያሒድ አስታዉቆ ነበር።ይሁን እንጅ ለሩጫዉ የሚሆን ትሸርቶችን አትሞ ለሯጮች ለማደል ሲባል ዉድድሩ ካንዴም ሁለቴ ተራዝመዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:28

«ለወገኔ እሮጣለሁ» ሩጫ

ዉድድሩ በፀጥታ ምክንያት በስምንት ከተሞች እንዳይካሔድ የሐገርቱ የደህንነት መስሪያ በት በመጠየቁ የአዘጋጆች ኮሚቴ አባላት በጥያቄዉ ላይ እየተወያዩ በመሆናቸዉ ለመራዘሙ ምክንያት መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ማስታወቃቸዉን  ዘግበን ነበር።

አሁን የዉድድሩ ዝግጅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፣ ምን ያህል ገቢ እንደተሰበሰበ የኮሚቴዉ አባል የሆኑት አቶ ገመዳ ኦልአና ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በጤና ምክንያት መሮጥ ከማይችሉት ዉጭ ፆታ እና እድሜን ሳይለይ አዲስ አበባን ጨምሮ በ20 የኦሮሚያ ዞኖች 150ሺ ሰዎችን በዉድድሩ  ለማሳተፍ ዕቅድ እንዳላቸዉ የአሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሐላፊ እና የኮሚቴዉ ሰብሳቢ አቶ ሞቱማ ተመስገን ለይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ከተሳታፍዎቹ ዉስጥ ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ኢብራህም ጄይላን፣ አትሌት ስለሺ ስህን፣ አትሌት  ገንዘቤና አትሌት ጥሩኔሽ ዲባባን  ጨምሮ ሌሎችም እንደሚሳተፉ ገልፀዋል።

ሩጫዉ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ክልሎች ለማኪያሔድ ዝግጅት ኢያደረጉ እንደሚገኙ አቶ ሞቱማ ይናገራሉ።


ይሁን እንጂ ሩጫዉ እንዲካሄድ ከታቀደባቸዉ 22 ከተሞች ዉስጥ ቢያንስ ስምንት በሚሆኑት ከተሞች ላይ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ውድድሩ ይካሄድ፤ አይካሄድ በሚለዉ ጉዳይ ኮሚቴዉ እና የፀጥታ አካላት ዉይይት በማድረግ ላይ እንደነበሩ ከዉስጥ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አቶ ሞቱማ ግን የደረሰን ጥያቄ የለም  ይላሉ።

ገንዘቡ ከተሰበሰበ በኋላ የተፈናቀሉትን ለመርዳት ለተቋቋመ ለሌላ ኮሚቴ እንደሚሰጥም አቶ ገመዳ አክሎዉ ገልፀዋል።

 መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic