የተመ የልማት መረሃ-ግብር ዓመታዊ ዘገባ | ዓለም | DW | 24.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የተመ የልማት መረሃ-ግብር ዓመታዊ ዘገባ

የተመድ የልማት መረሃ ግብር በምህፃሩ UNDP የ2014 ዓመታዊ ዘገባ ሥራና ማኅበራዊ ዋስትና፤ ለአፍሪቃ እድገት ያመጣል ይላል። ይህች አህጉር ግን አሁንም ቢሆን አደጋ የተደቀነባት ናት። ድርጅቱ በመጀመርያ ገጹ ይፋ ያደረገዉ ዘገባ ተስፋ ይሚሰጥ ነዉ።

የአፍሪቃ የኤኮኖሚ እድገት፤ የኑሮ ምቾት፤ የሚታይበት፤ እንዲሁም ባለፉት ሶስት ዓመታት፤ በገቢ፤ በጤና አጠባበቅ እና በትምህርት ሥልጠና አመርቂ ዉጤትን ማሳየትዋን የተመድ የልማት መረሃ-ግብር የአፍሪቃዉ ክፍል ተጠሪ አብዱላዬ ማር ዲዬ ገልፀዋል። ዘንድሮዉን የተመ የልማት መረሃ-ግብር ዓመታዊ ዘገባ፤ የዶቼ- ቬለዋ ሽቴፋኑ ዱክሽታይን ያቀረበችዉን ዘገባ፤ አዜብ ታደሰ እንዲህ አጠናቅራዋለች።


የመንግሥታቱ ድርጅት የልማት መረሃ -ግብር፤ ሩዋንዳ እና ኢትዮጵያ ፈጣን እድገትን ማሳየታቸዉን ገልጾአል። ሁለቱ ሃገራትን በመከተል አንጎላ፤ ብሩንዲ እና ሞዛንቢክ እድገት ያሳዩ የአፍሪቃ ሃገሮች መሆናቸዉን የተመድ የልማት መረሃ-ግብር የአፍሪቃዉ ክፍል ተጠሪ አብዱላዬ ማር ዲዬ ገልፀዋል። ይሁንና በእነዚሁ ሃገራት ሌሎች ችግሮች እንደሚታዩ ዘገባዉ ይፋ አድርጎአል። ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገሮች በሃብታሙ እና ደሃዉ ማኅበረሰብ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ይታያል። በእነዚህ ሃገራት 585 ሚሊዮን ህዝብ ማለትም፤ 72 በመቶዉ ህዝብ ህይወቱን የሚገፋዉ በድህነት ነው። አልያም ለድህነት ተጋልጠዋል።
በሃገራቱም ሆነ በየእንዳንዱ ማኅበረሰብ ላይ በቋሚነት ለቀጠለውና እና እየተባባሰ ለሄደው ድህነት ዋና ምክንያት ህዝቡ የኑሮ ዋስትን ማጣቱ ነዉ ሲሉ የተመድ የልማት ድርጅት ዳሪክተር ካሊድ ማሊክ ገልፀዋል። ግን ለዚህ ተጠያቂዉ ማን ይሆን ማሊክ መልስ አላቸዉ። « ሰዎች ለችግሩ የሚጋለጡበት ዋና ተጽዕኖ የሚፈጠረዉ፤ በሚኖራቸዉ የጤና አገልግሎት እና የትምምህርት ደረጃ ነዉ። የተሻለ የትምህርት ሥልጠና ካላቸዉ፤ ሃብት ይኖራቸዋል፤ ችግራቸዉንም አስተማማኝ በሆነ መንገድ ይቋቋማሉ። ከዚህ በተጨማሪ በርግጥ በሃገራቸዉ የመጡት ከአናሳ ጎሳ መሆኑም አንድ ሚናም ይጫወታል»
ተገን ጠያቂዎች፤ ሴቶች፤ ህጻናት፤ አረጋዉያን እና የገጠሩ የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ለመገለሉ አደጋ ተጋልጠዉ ይገኛሉ።

Nigeria: Blick auf Lagos

ናይጀርያ ሌጎስ ከተማ

እነዚህ የማኅበረሰብ ክፍሎች በህይወታቸዉ ችግር ከገጠማቸው ፤ ከኅብረተሰቡ ድጋፍን ስለማያገኙ ሥራቸዉን ያጣሉ፤ ቶሎም ለህመም እና ለበሽታ ይጋለጣሉ።
«ከዓለም ህዝብ ወደ 80 በመቶ የሚሆነዉ ማኅበራዊ ዋስትና የለዉም፤ 12 በመቶዉ ደግሞ መፍትሄ ባላገኘ ከፍተኛ ረሃብ ይሰቃያል፤ ከዚህ መካከል 1,5 የሚሆነዉ ሰራተኛ ህዝብ ደግሞ ለጤና አደገኛ በሆነ ከባድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል»
በኢንዱስትሪ ከበለፀጉት ሃገራት ይልቅ አዳጊዎቹ ሃገራት ማህበረሰብ፤ በህዝብ ብዛት መንስኤ በድህነት ያጠቃል ። UNDP ይፋ በአደረገዉ ጥናታዊ ዘገባ የ187 ሃገራት እድገት ገምግሞ መዘርዝር ያወጣ ሲሆን፤ በዚህ ጥናታዊ ግምገማ እጅግ ከፍተኛ እድገትን ያሳየችዉ ሃገር፤ በአንደኛ ደረጃ ኖርዌይ፤ በሁለተኛ ደረጃ አዉስትራልያ፤ በመለጠቅ፤ ስዊዘርላንድ በሶስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች። በአንጻሩ በመዘርዝሩ የመጨረሻ ረድፍ ላይ የተቀመጡት ከሳሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ ሃገሮች ሲሆኑ፤ በማዕከላዊ አፍሪቃ የምትገኘዉ ሃገር ኒጀር የመጨረሻዉን ቦታ ይዛ ትገኛለች።
በበርሊን በሥነ-ሰዉ ተዋልዶ ጥናት እና ልማት ተቋም ባለሞያዋ ሩት ሙለር እንደሚሉት የህዝብ ቁጥር መጨመር የድህነት መንስኤ ነዉ፤
« በተለይ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ ሃገራት በከፋ ድህነት ዉስጥ ይገኛሉ። በሌሎች ሃገራትም ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር መጨመር ይታያል። ይህን ህዝብ ለመመገብ ደግሞ ከባድ ሁኔታ ነዉ። የህዝብ ቁጥር በጨመረ መጠን፤ አቅርቦቱም መጨመር ይኖርበታል»
በአሁኑ ወቅት በአፍሪቃ ሃገራት የኤኮኖሚ እድገት ቢታይም፤ ለበርካታ ህዝቦች የሚዉለዉ የምግብ አቅርቦት፤ የትምህርት ስልጠና እና የጤና ጥበቃ ፍጆታ፤ ሃገራቱ ኤኮኖሚ ላይ ተፅእኖ አሳድሮአል፤
ማኅበረሰባዊ ድጋፍ የሰዎችን ህይወት ወይም ዋስትና ለመስጠት የሚያገለግል መሳርያ መሆኑን የተመድ የልማት ዓመታዊ ዘገባ ዳሪክተር ካሊድ ማሊክ ገልፀዋል። እንደ ማሊክ «ታዳጊ ሃገሮች 3 እስከ 5 በመቶ የሚሆነዉን የገቢ ምንጫቸዉን ለማኅበረሰብ ድጋፍ ግልጋሎት መመደብ ይኖርባቸዋል። ይህን ቢያደርጉ ሃገራቱ የሚኖራቸዉ ጥቅም ከፍተኛ ይሆናል።

Khalid Malik

የተመድ የልማት ድርጅት ዳሪክተር ካሊድ ማሊክ

ምክንያቱም መዋለ ንዋይን ማፍሰስ የበለጠ ምቾትን በማምጣቱ ነዉ፤ ይህ አይነቱ አካሄድ በኤኮኖሚ ምሁራንም የተረጋገጠ ነዉ።»
የሥነ-ህዝብ ጉዳይ ምሁርዋ ሩት ሙለር በበኩላቸዉ፤ በዚህ ጉዳይ አይስማሙም። ዋናዉ ነገር ይላሉ ሩት ሙለር በመቀጠል፤
« ህዝብ ለረጅም ግዜ ወደ ተባባሰ ድህነት እንዳይገባ ለመከላከል ሰፋ ያለ ዋስትና በእቅድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይህ ማለት አንድ ቤተሰብ ገቢ አገኛለሁ፤ ልጆቼን ማሳደግ፤ ጤናዩን መጠበቅ እችላለሁ፤ ሲል ነዉ፤ ይህ እቅድ ሰራ የምንለዉ። በመጀመርያ ይህ ከሆነ ነዉ የኑሮ ዋስትና ሊኖር የሚችለውና እድገት አለ የምንለዉ»
አፍሪቃ ሃገራት ወደፊት እዳይራመዱ ሳንክ የሚሆንባቸዉ ዋናዉ ነገር በከፍተኛ ሁኔታ የወሊድ ቁጥር መጨመር ነዉ። የወሊድ ቁጥር ከቀነሰ በማኅረሰቡ የተወሰነ እድሜ ክልል ያሉ ነዋሪዎች ቁጥር ይጨምራል፤ በዚህም ሠርቶ የሚተዳደረዉ ህብረተሰብ ቁጥር ከፍ ብሎ ይገኛል። ሩት ሙለር በመቀጠል ፤ « ይህ ሰርቶ የሚተዳደረዉ ኅብረተሰብ ቁጥር ከጨመረ እና ለሱ የሚሆነዉ በቂ የስራ ቦታ ካለ በአንድ ግዜ እድገትን የሚያራምድ አምራች ኃይል ይገኛል። በዚህ ላይ ደግሞ የትምህርት ሥልጠና ላይ መዋለ ንዋይ ካፈሰሰ የኤኮኖሚ እድገትን የሚፋጠንበት ሁኔታ ይፈጠራል»
አንድ ኅብረተሰብ ዋስትና እንዲያገኝ ያለበት ሃገር እድገት ብቻ ወሳኝነት የለዉም። የፋይናንስ ቀዉስ፤ የዓየር ንብረት መለዋወጥ ፤ የስድተኞች ጎርፍ፤ የመሳሰሉት ችግሮች የሚከሰቱት በዓለማቀፍ ቀዉስ ነዉ ። ይህ አደጋ ደግሞ በተለያዩ ሃገሮችና አህጉሮች የሚገኘዉን ህዝብ ሊያጠቃ ይችላል።

Ruth Müller Institut für Bevölkerung und Entwicklung

በበርሊን ሥነ-ሰዉ ተዋልዶ ጥናት እና ልማት ተቋም ሩት ሙለር

በዚህም ምክንያት በነዚህን ችግሮች መከላከል የሚቻለዉ ዓጽናፋዊ የሆነ መፍትሄ በማስገኘት ብቻ ነዉ መሆኑን የተመድ ዓመታዊ ዘገባ ያትታል። ለነዚህ ችግሮች የሚቀርቡት መፍትሄዎችም የአጭር ግዜ ብቻ መሆን የለባቸዉም።
ለምሳሌ በመካከለኛዉ አፍሪቃ የምትገኘዉ ኒጀር በከፍተኛ ድርቅ ምክንያትለአስጊ ረሃብ ተጋልጣለች። የኒጀር ጎረቤት በሆነችዉ ማሊ ደግሞ እስላማዊ ታጣቂዎች በስልጣን ሽኩቻ ባስነሱት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በረሃብ አደጋ ላይ ወደምትገኘው ወደ ኒጀር በመፍለስ ላይ ናቸዉ።
በርካታ ሃገራትን ያቀፉ ድርጅቶች ለምሳሌ በኢንዱስትሪ ያደጉና በማደግ ላይ ያሉ ሃገሮች የተሰባሰቡበት ቡድን 20ን የመሳሰለት ስብስቦች ይህን አይነቱን አፅናፋዊ ችግር ለመፍታት ትልቅ ሃላፊነት መዉሰድ ይጠበቅበባቸዋል ይላል የዘንድሮዉ የተመድ ዓመታዊ የልማት ዘገባ ያመላክታል።

አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic