የተ.መ.ድ ጉባኤና የባራክ ኦባማ ንግግር | ዓለም | DW | 26.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የተ.መ.ድ ጉባኤና የባራክ ኦባማ ንግግር

ኦባማ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር በተለይ ኢራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳትሆን አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ። ሙስሊሞችን ባስቆጣው ፊልም ምክንያት በሙስሊም አገራት በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ የተሰነዘሩትን ጥቃቶችና የተከተሉትን አመፆችም በዲሞክራሲ ላይ ያነጣጠሩ በማለትም አውግዘዋል ።

ኒውዮርክ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው 67 ተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ የመንግሥታት መሪዎች ዛሬም ንግግር ማድረጋቸውን ቀጥለዋል ። ትንንት በድርጅቱ አመታዊ ጉባኤ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ካደረጉት መሪዎች አንዱ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማ ናቸው ። ኦባማ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር በተለይ ኢራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳትሆን አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ። ሙስሊሞችን ባስቆጣው ፊልም ምክንያት በሙስሊም አገራት በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ የተሰነዘሩትን ጥቃቶችና የተከተሉትን አመፆችም በዲሞክራሲ ላይ ያነጣጠሩ በማለትም አውግዘዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተ ዲሲው ዘጋቢኢችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ

Audios and videos on the topic