የተመድ የጤና ቡድን በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 12.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የተመድ የጤና ቡድን በኢትዮጵያ

ተቀማጭነዉ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ የሆነዉ የተመ የጤና ቡድን በእንግሊዝና ምህፃሩ UNIT-Aid በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን በሚመለከት ከሀገር ዉስጥ ባለሙያዎች ጋ ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛል።

ቡድኑ በተለይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ የሚገኙት የTB፣ የHIV ኤይድስና የወባ ወረርሽኝ የሚገኙበትን ደረጃ በመመልከትም የምርምር ዉጤት የሆኑ ዘመናዊ መድሃኒቶችና ለምርመራ የሚዉሉ መሣሪያዎች የሚገኙበትንም መንገድ ይነጋገራል። በተለያዩ ስፍራዎችም የሚገኙ የጤና ጣቢያዎችን ና ሆስፒታሎችንም መጎብኘቱን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic