የተመድ እና የማሊ ተልዕኮ ጉዳይ | አፍሪቃ | DW | 01.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የተመድ እና የማሊ ተልዕኮ ጉዳይ

የተ,መ,ድ ፀጥታ ምክር ቤት በሰሜናዊ ማሊ አንድ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል የሚሰማራበትን ዉሳኔ እንዲያመቻች የዓለሙ መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ

የተ,መ,ድ ፀጥታ ምክር ቤት በሰሜናዊ ማሊ አንድ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል የሚሰማራበትን ዉሳኔ እንዲያመቻች የዓለሙ መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባንኪሙን ባለፈዉ ረቡዕ ሃሳብ አቅርበዋል። ይሁንና ዋና ፀሃፊዉ ድርጅታቸዉ ለዚሁ በማሊ ይሰማራል በሚባለዉ ተልዕኮ የገንዘብ ርዳታ ማድረግ አለማድረጉን ሳይጠቅሱ ነበር ያለፉት። በማሊ እንዲጀመር የተፈለገዉን የሰላም ተልዕኮ ከሌሎች የተ,መ,ድ ሰላም ማስጠበቅያ ወይም ማስከበርያ ተልዕኮዎች ልዩ የሚያደርገዉ፤ በዉግያ ተግባር ተሳታፊ መሆን መቻሉ መሆኑን የዓለሙ መንግስታት ድርጅት ዲፕሎማቶች ገልጸዋል። የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ፤ እስከ መጭዉ ታህሳስ አጋማሽ ድረስ፤ ይኸዉ የአፍሪቃ ህብረት የሰላም ተልዕኮ በማሊ የሚሰማራበትን ረቂቅ ዉሳኔ  እንዲያወጣ ፈረንሳይ ጠይቃለች።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰሜናዊ ማሊን በጠቅላላ፤ ከፅንፈኞቹ አማፅያን ቁጥጥር፤  ነፃ መሆን አለበት በሚለዉ ሃሳብ ላይ ይስማማሉ። ይን ለማሳካትም፤ የምዕራብ አፍሪቃ መንግስታት  የኢኮነሚ ማህበረሰብ በኢንግሊዘኛ ምህፃሩ ECOWAS - 3300 ወታደሮችን ወደ ማሊ ለመላክ ፍላጎቱን ካሳየ ብዙ ወራት አልፈዋል። ለዚሁ የምዕራብ አፍሪቃ መንግስታት  የኢኮነሚ ማህበረሰብ ECOWAS ጦር ፤ ወታደሮች የሚያዋጡት ሀገራት፤ ናይጀሪያ፤ሴኔጋል፤ ኒጀር፤  ቡርኪናፋሶ፤ ጋና ና ቶጎ ናቸዉ። 

አርያም ተክሌ

መስፍን መኮንን 

Audios and videos on the topic