የተመድ በኢትዮጵያ የመብት ጥሰትን ለማጣራት የጀመረው ጥረት | ኢትዮጵያ | DW | 11.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የተመድ በኢትዮጵያ የመብት ጥሰትን ለማጣራት የጀመረው ጥረት

በኦሮምያ እና በአማራ ክልል ሰሞኑን የተቀሰቀሱ ተቃዉሞዎችን ለመደፍለቅ፤ የኢትዮጵያ መንግስት የፀጥታ ሐይላት በወሰዱት ርምጃ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸዉን እና በሺ የምቆጠሩ ደግሞ መታሰራቸዉ እየተዘገበ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:20

ሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በእንግሊዘኛው ምህጻር (UNHRC) በሁለቱም ክልሎች ተቃዉሞ በተካሄደበት ወቅት የፀጥታ ሃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይል ተጠቅመዋል ተብሎ የቀረበባቸውን ክስ ለማጣራት ዓለም ዓቀፍ ታዛቢዎች ግጭት ወደ ተካሄደባቸው አካባቢዎች እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው ጠይቋል።

በኦሮምያና በአማራ ክልል ብዙ ሰዎ መገደላቸዉ እና መታሰራቸዉን በተመለከተ በጣም የሚያሳስብ ዘገባዎች እየወጡ ቢሆንም ኢንቴርኔት በመዘጋቱና ይህን ጉዳይ ማጣራት የሚችሉ የሲቪክ ማህበራት ባለመኖራቸዉ ዘገባዎቹን ለማጠራት አስቸጋር ሆኖዋል ሲሉ የኮምሽኑ ቃላቀባይ ራቪና ሻምዳሳኒ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ተቃዉሞዉና ግድያዉ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲካሄድ እንደነበረ ዘገባዎች ቢያመለክቱም ኮሚሽኑ አሁን የዓለም ዓቀፍ ታዛቢዎች ለመላክ ያነሳሳበት ምክንያት ምንድነዉ ተብሎ ሲጠየቁ፣ «ምክንያቱም በትክክለኝነት ይህ ጉዳይ ለወራቶች ሲካሄድ ቆይተዋል፣ በጥር ወርም የተቃዋሚዎች መሞት፣ መታሰርና ሌሎች ጉዳቶች በፀጥታ ሃይሎች ሲደርስባቸዉ እንደነበር ዘገባዎች ነበሩ። ግን አብሶ የሚያሳስበዉ ጉዳዩን ለመመርመርና ተጠያቂነትን ለመማምጣት እዉነተኛ የሆነ ሙከራ አልነበረም። አሁን ተመሳሳይ ዘገባዎች በሚመጡበት ጊዜ ጉዳዩ በጣም የሚያስፈራ በመሆኑና ባለፈዉም ቅጣት ሳይተላለፍ በመቅረቱ ነዉ።»

ኮሚሽኑ በጉዳይ ላይ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ጠቅሶ ታዛቢዎች ተልኮ ምን ሊሆን እንደሚችል ራቭና እንዲህ ይላሉ፣ «የተልኮዉ አላማ ወደ ቦታዉ ሄዶ በገለልተኝነት ጉዳዩን ማጣራት ነዉ። የሞቱትን ቁጥር በተመለከተ ብዙ የተለያዩ ግምቶች ስላሉ፣ ከመንግስት ጋራ ወይም ከተቃዋሚዎች ጋር ያልተገናኙ ገለልተኛ የሆኑ አጣሪዎች ልኮ መሬት ላይ የሆነዉን ነገር እንድያጣሩ ማድረግ ነዉ።»


እስካሁን በምንግስት በኩል ምንም ምላሽ እንዳላገኙ ግን አዎንታዊ ምላሽ እንደማያገኙ ተሳፋ አለን ይላሉ ቀልአቀባዩዋ። በመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ጽ/ቤት የህዝብ ግኑኝነት ሐለፊ አቶ መሃመድ ሳይድን ብዙም መረጃ እንዴሌላቸዉ ተናግሮ መንግስት በራሱ ችግሩን ይፈታል ስሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ሌሎች እንደነ ሁዩማን ራይትስ ዋችና አምንስቲ እንቴርናሽናልን የመሳሰሉ የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም የግድያም ሆነ የእስራት ጉዳዮችን ቦታዉ ላይ ሆኖ ለማጣራት ቢሞክሩም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ፍቃድ አለገኘንም ስላሉ የኮሚሽኑም ጥያቄ ምን ያህል ሊሳካ ይችላል ብለን ራቪና ሲጠየቁ፣ «ይህ ቅጣት አይደልም፣ አገርቱን ለመጉዳት የተወሰደ ርምጃ አይደልም። የተፈ,ጠረዉን በገለልተኝነት ለማጣራት እና ለመመርመር ነዉ። ስለዚህ ለአገርቱ መንግስትም ፍትህ እንዲከበር ለማድረግ ትልቅ እድል ነዉ። ይህም የተከሰተዉ እዉነታ ታርካዊ መዝገብ እንዲኖር ያረጋግጣል፤ እንድሁም ፍትህ ጉዳዮች እንዳያመረቅዝ ያደርጋል። እንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ ከቀጠለ፣ በጥር ወር እንደተደረገዉ፣ ብዙ ነገሮች እንዲገነፍሉ ያደርጋል፣ ብዙ አለመረገጋት፣ ተቃዉሞና ግጭቶች ይኖራል። ስለዚህ ጉዳዩን ገለልተኛ በሆነ አካል ማጣራት የአገርቱ መንግስትና ህዝብ ፍላጎት መሆን አለበት።»


ጉዳዩን በተመለከተ ፌስቡክ ላይ አስተያየት ከሰጡን ዉስጥ «ኣይሳካም መሳካትም የለበትም!!! ይህ የውስጥ ጉዳያችን በራሳችን እንፈተዋለን» የሚሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ «የምርጫ ኮሮጆ ሠርቆ ያለሀፍረት "መቶ በመቶ አሸንፌያለሁ"ያለው እንዴት ብሎ ይፈቅዳል?» ብሎ ከጠየቁ በዋላ «ህዝቡ ግን በተባበረ ክንድ ወያኔን ማንበርከክ ይችላል ይላሉ።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ

Audios and videos on the topic