የተመድ መታሰቢያ ዕለታትና አመታት | ዓለም | DW | 13.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የተመድ መታሰቢያ ዕለታትና አመታት

ችግሩ ሰዎች ለጉዳዩ ደንታ ሥለሌላቸዉ አይደለም።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ብዙ ጉዳዮችን ባንዴና በእኩል ጊዜ ለማስተዋወቅ መሞከሩ እንጂ

default

የተመድ ጠጉ

07 01 10

የጎርጎሮስያኑ 2010 ብሪታንያ ወይም ሌላ ሥፍራ ምርጫ የሚደረግበት፥ደቡብ አፍሪቃ የአለም እግር ኳስ የዋንጫ ዉድድር የምታስተናግድበት፥ የጨረቃ ግርዶሽ የሚታይበት፥ የናሳ አዲስ ፕሮጄክት የሚቀረፅበት አመት ብቻ አይደለም።የተባበሩት መንግሥታት ሁለት አለም ቀፍ ጉዳዮች የሚታሰቡበት አመትም ጭምር እንጂ።የመታሰቢያዎቹ አመታት ምን ያሕል ዉጤታማ ናቸዉ? ትኩረቱን ይስባሉ ተብሎ የሚጠበቀዉ ሕዝብስ ያዉቃቸዉ ይሆን?።ታምሲን ወከር የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።

ወንድ፣-«ድሕነትና ረሐብን የመዋጊያ አለም አቀፍ አመት ይመስለኛል።»
ሴት፣-«አዝናለሁ የማዉቀዉ ነገር የለም»
ወንድ፣- «እንጃ»
ሴት፣- «ምናልባት የጉዞ ወይም የመራቅ አለም አቀፍ አመት ይሆን?»
ወንድ፣-«ቆይ፥ ቆይ---ኦ አላዉቀዉም»
ሴት፣-«አዝናለሁ ምንም ፍንጭ የለኝም»

በርግጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 2010ን የሁለት ማለትም የባሕል ዳግም መቀራረቢያ እና የብዝሐ-ሕይወት መታሰቢያ ብሎ ሰይሞታል።አሁን አይደለም አመቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ እንኳን አብዛኛዉ ሰዉ አላማቸዉን መገንዘቡ ያጠራጥራል።

ችግሩ ሰዎች ለጉዳዩ ደንታ ሥለሌላቸዉ አይደለም።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ብዙ ጉዳዮችን ባንዴና በእኩል ጊዜ ለማስተዋወቅ መሞከሩ እንጂ።ባለፈዉ አመት ሰወስት አለም አቀፍ ዕለታት ነበሩ።ዘንድሮ ሁለት ናቸዉ።በ2011 ሁለት ይኖራሉ።ይሕ የፖለቲካ ሳይንቲስት ዮሐንስ ፋርቪክ እንደሚሉት

UN Jahr der Versöhnung Mitmachen

የተመድ የትብብር መታስቢያ ዕለት አርማ

በጣም ብዙ ነዉ።

«የአለም አቀፍ አመታትና ዕለታት ቁጥር በጣም እየናረ መምጣቱን አስተዉለናል። የሚነሱት ጉዳዮች በበዙ ቁጥር ሰዉ ምን እንደሆኑ በትክክል መረዳት ያቅተዋል።»

የመጀመሪያዉ አለም አቀፍ መታሰቢያ አመት በ1957 ለጂኦ ቪዝክስ መታሰቢያ የዋለዉ ነበር።እስከ ዘጠናዎቹ ድረስ ቀስ በቀስ እየጨመሩ መጥተዉ ባለፈዉ አስርት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀን መቁጠሪያዎች ለምንምና ለሁሉም ነገር መታሰቢያ ነት ተጨናነቀ።ምክንያቱ እንደገና ፋርቪክ፥-

UN Jahr der Versöhnung Quiz

የተመድ የጥያቄ መታሰቢያ ዕለት

«የተወሰኑ ጉዳዮች ርዕሥ እንዲሆኑ ግፊት የሚያደርጉ የአባል ሐገራት ቡድናት በመኖራቸዉ ነዉ።እና ማነዉ የሚቃወማቸዉ።እኔ የጠቅላላ ጉባኤዉ አባል ብሆንና የሆነ ሐገር ለድንች መታሰቢያ አመት ይሰየም ቢለኝ-ምናልባት እሺ ነዉ የምለዉ።ማንም አይገዱም።ግን የጉዳዮችን መጨናነቅ ያስከትላል። እና ሁሉም ይሳከራል።በጣም ሲበዛ ደግሞ ስሜት አይሰጥም»

የጀርመኑ የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር የበላይ ቤአት ቫግነር-እንደሚሉት አሁን የሚታየዉን መሳከር ለማስቀረት አለም አቀፉ ድርጅት በ1980ዎቹ መጠንቀቅ ነበረበት።ጠቅላላዉ ጉባኤ አለም አቀፍ አመታትና ዕለታት ለመታሰቢያነት የሚሰየሙበት ሕግ አፅድቋል።ብዙ ጊዜ ግን ሕጉን ራሱ አያከብረዉም።

የመታሰቢያ እለቶች በጠቅላላዉ ጉባኤ ቢወሰኑም ገቢራዊነታቸዉ፥ የመንግሥታት፥ የመያዶችና የሲቢል ማሕበራት ጥገኛ ነዉ።አብዛኞቹ መያዶች ደግሞ ዘመቻና ቅስቀሳቸዉን ለድፍን አመት የሚቀጥሉበት ገንዘብ የላቸዉም።ሥለዚሕ በጀርመን የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ተጠሪ ዳፊድ ዳንኢሎ ባርቴልት እንደሚሉት መያዶች ከአመታቱ ይልቅ በዕለታቱ ላይ ማተኮሩን ይመርጣሉ።

መታሰቢያዎቹ ዕለታቱም ራሳቸዉ የአመታቱን ያክል መብዛታቸዉ ነዉ-ጭንቁ።ከሰባ የሚበልጡ የመታሰቢያ ዕለታት አሉ።እና ይላሉ ባርቴልት ዕለታቱም «ከቁቁጥር እየወጡ ነዉ»
«በዛሬ ጊዜ ለያንዳዱ አካልና ነገር አለም አቀፍ መታሰቢያ ዕለት አለ።አለም አቀፍ የመምሕራን፥ የአካለ ሥንኩላን መታሰቢያ ዕለታት አሉ።እነዚሕና መሰሎቹ ብዙ ጊዜ የመገኛ ዘዴዎች ሽፋን የማያገኙ አነሳ ቡድናት ትኩረት እንዲስቡ ሥለሚያደርጉ ጠቃሚዎች ናቸዉ።ግን ደግሞ አለም አቀፍ የጥንቸል መታሰቢያ ዕለት፥ አለም አቀፍ የብርቱካን መታሰቢያ

UN Jahr der Versöhnung Warheit

የተመድ የእዉነት መታሰቢያ ዕለት አርማ

ዕለት አለ።እኚሕ አለም ቀናትን እንዳያሰለቹ እፈራለሁ።»

አብነቱ ቫግነር እንደሚሉት አለም አቀፉ ድርጅት በ1980 ዉሳኔዉ መመለስ ነዉ።ድርጅቱ ዛፎችን ከእንጨት መለየት መፍቀዱ ወደፊት የሚታይ ነዉ-የሞሆን።ላሁኑ ግን ሁሉም ብዝሐ ሕይወት ነዉ።

ታማሲን ዎከር/ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic