የተመደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ጉብኝት በኢትዮጵያ  | ኢትዮጵያ | DW | 05.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የተመደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ጉብኝት በኢትዮጵያ 

ኢትዮጵያ ዉስጥ ለተከታታይ ወራት በተደረገዉ ሕዝባዊ አመፅ የደረሰዉን ጉዳት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች እንዲያጣሩት የድርጅቱ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የበላይ ኃላፊ በድጋሚ ጠየቁ። ኮሚሽነሩ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን «አጣራሁ» ያለዉን ዘገባ ትክክለኝነት ኮሚሽናቸዉ እየመረመረ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:45

ሰብአዊ መብት

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛይድ ራኣድ ኣል ሁሴን በመንግሥት ጋባዥነት በኢትዮጵያ ያደረጉት የሦት ቀን ጉብኝት ዛሬ አጠናቀቀዋል።ዛይድ ራኣድ ኣል ሁሴን በአገሪቱ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች ሲካሄዱ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰት በሚመለከት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸዉን የኮሚሺነሩም ቃል አቀባይ ሩዝ ማርሻል ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ኮሚሽነር ሁሴን የተቃዋሚ ፓርት አመራሮችንና እስረኞች አግኝተዉ እንዳነጋገሩም ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ያነሳሳቸዉም በአገሪቱ የታወጀዉን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተከትሎ ያለዉ የሰብአዊ መብት አያያዝ  ጉዳይ አሳስቧቸዉ እንደ ሆነ ማርሻል ይናገራሉ። ቆይታቸዉን በተመለከተም እንዲህ ብለዋል፣ «በጣም ጥሩ ጉብኝት ነበር። ወደ እስር ቤት በመሄድ ከተለያዩ እስረኞች ጋር ተነጋግረናል። ኮሚሽነሩም ከአንድ እስረኛ ጋር፣ ምንም ታዛቢ ወይም ምስክር በሌለበት ረጅም የሆነ የግል ዉይይት አካሂደዋል። እኔም ደግሞ ከሌላ እስረኛ ጋር ተነጋግሬያለሁ። እሱም አስገራሚ ነበር። ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርትና የገዥዉ ፓርት አመራሮች ጋርም ተነጋግረናል። ከመብት ተሟጋችና ከሲቭል ማህበረሰቡ የተወጣጡ ግለሰቦች ጋርም ተወያይነተናል። ዉይይቱም ግልፅነት የሞላበት ነበር፣ ይህም አዎንታዊና የሆነ ተስፋ ሰጭ እንደሆነ ነዉ።»

ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና እስረኞች ጋር የተደረገዉ ዉይይት ይዘቱን የተጠየቁት ቃል አቀባይዋ «ምስጢራዊ» በመሆኑ ለመናገር ፍቃደኛ አልሆኑም። 
ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተደጋጋሚ የምትወቀስ አገር መሆኗን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ይህ ሆኖ እያለ ኮሚሽነሩ በቆይታቸዉ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን «በመጠበቅና በማስተዋወቅ» የኮሚሽኑ አጋር አገር ናት ማለታቸዉ አነጋጋሪ ሆኖዋል። ግን የኮሚሽነሩ ቃለ አቀባይ ሩዝ ማርሻል የአባባል «ትርጓሜ» ጥያቄ ነዉ ይላሉ።

ሩዝ በመቀጠልም«እዚህ ጋር የትርጓሜ ጥያቄ አለ። በአለም ያሉት ሁሉም አገራት ዉስጥ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን ማስጠበቅ ኃላፊነቱ የማነዉ? የተመደ የዉጭ አካል አይደለም፣ መንግስት ነዉ። በሁሉም ጉዳዮች የሰብዓዊ መብት ይዞታን ለማስጠበቅ መንግስት ኃላፍነቱን ወስዶ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር ይሠራሉ። የትኛዉም መንግሥት ንፁሕ ወይም የተሟላ ሪኮርድ የለዉም፣ እኛም ለመንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሠራዉን ስራ አንደብቀለትም።»

በኮሚሽነሩን ጉብኝትና በአገሪቱ ያለዉ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ በፌስ ቡክ ገጻችን አስተያየት ከሰጡን ዉስጥ፣ አገሪቱ የራሷን ችግር በራሷ ትፈታለች ያሉን ሲኖሩ፣ ሌሎች ደግሞ ኮሚሽነሩ ጉብኝት ወይም ዉይይት መሬት ላይ የሚቀይረዉ ነገር የለም የሚሉ አስተያየቶችን ሰንዘረዋል። 

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ 


 

Audios and videos on the topic