የቦትስዋና ምርጫና የፕረሱ ፈተና | አፍሪቃ | DW | 24.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የቦትስዋና ምርጫና የፕረሱ ፈተና

ስለአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ሲወሳ፣ የውጭው ዓለም ከመቅጽበት የሚያስበው ስለጦርነት ፤ ቀውስ የተፈጥሮ አደጋና የመሳሰለው ነው። አፍሪቃን አጨለምው ለሚመለከቱ ወገኖች የሆነው ሆኖ ፣ የቦትስዋና ይዞታ አስተሳሰባቸው መሠረተቢስና አሉታዊነት የተሞላ መሆኑን

ያጋልጥባቸዋል። ቦትስዋና ለአፍሪቃ ሃገራት ሁሉ ግንባር ቀደም አርአያ ናት። በቆዳ ስፋት ከፈረንሳይ የማታንሰው ሀገር 2 ሚሊዮን ኑዋሪዎች ብቻ ነው ያሏት።

ከእነዚህም መካከል ለምርጫ ብቁ የሆኑት 800,000 ው ፣ ዛሬ አደባባይ በመውጣት ፣ አዲስ የሕዝብ እንደራሴዎች በተዘዋዋሪ መንገድም አዲስ ፕሬዚዳንት ጭምር ይመርጣሉ።አሁን የፕሬዚዳንትነቱን ሥልጣን የያዙት ኢያን ካማ ዳግም ለመመረጥ ለመመረጥ ሁኔታው ይበልጥ አመቺ ሳይሆንላቸው አልቀረም። ስለቦትስዋናው ምርጫና ነጻው ፕረስ ቅር ስለተሰኘበት ሁኔታ ከደቡብ አፍሪቃ የዶቸ ቨለ ባልደረባ ፣ ያን ፊሊፕ ሹዑልተር ያሰናዳው ዘገባ---

ስለአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ሲወሳ፣ የውጭው ዓለም ከመቅጽበት የሚያስበው ስለጦርነት ፤ ቀውስ የተፈጥሮ አደጋና የመሳሰለው ነው። አፍሪቃን አጨለምው ለሚመለከቱ ወገኖች የሆነው ሆኖ ፣ የቦትስዋና ይዞታ አስተሳሰባቸው መሠረተቢስና አሉታዊነት የተሞላ መሆኑን ያጋልጥባቸዋል።

ስለአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ሲወሳ፣ የውጭው ዓለም ከመቅጽበት የሚያስበው ስለጦርነት ፤ ቀውስ የተፈጥሮ አደጋና የመሳሰለው ነው። አፍሪቃን አጨለምው ለሚመለከቱ ወገኖች የሆነው ሆኖ ፣ የቦትስዋና ይዞታ አስተሳሰባቸው መሠረተቢስና አሉታዊነት የተሞላ መሆኑን ያጋልጥባቸዋል።

ቦትስዋና ፣ የአፍሪቃ ስዊትስዘርላንድ የምትባል ናት። በክፍለ- ዓለሙ በአማካይ እጅግ ከፍ ያለ የወርም ሆነ የዓመት ገቢ ካላቸው ጥቂት የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች መካከል፣ የቦትስዋና ይገኙበታል። በሞ ኢብራሂም ድርጅት የመልካም አስተዳደር መለኪያ መሠረት ፤ ቦትስዋና 3ኛ ናት። በዓለም ውስጥ በአልማዝ ማዕድን ምርት የመጀመሪያውን ደረጃ ብትይዝም፤ የፖለቲካ መሪዎቿ የሀገርን ሀብት አጋብሶ አላግባብ በመበልጸግ አይታሙም። እንዲያውም ሃገሪቱ የምታገኘውን ገቢ ፤ ለዐሠርተ- ዓመታት ተምሳሌትነት ባለው መልኩ ለመሠረተ ልማትና ትምህርትን ለማስፋፋት ነው ያዋሉት። በብዙ ነገሮች በአርአያነት የምትተጠቀሰው ቦትስዋና አሁን አሁን የምትተችባቸው አንዳንድ ጉዳዮች ሳያጋጥሟት አልቀሩም። ከተቃውሞ ፓርቲዎች እንደሚሰማው ከሆነ ነቀፌታው የአሁኑ ፕሬዚዳንት የአምባገነንነት ባህርይ እያንጸባረቁ ነው ፣ ሙሰኛም ሆነዋል የሚል ነው። የቀድሞው የጦር ሠራዊት ጀኔራል ሒስ እንዲቀርብባቸው አይፈልጉም። ካማ ፤ ከምርጫ በፊት በቴሌቭዥን በሚካሄድ ክርክርም ፣ ስላልፈለጉ አልተገኙም። የሰውየው ሁኔታ ፣ «ሜጊ» የተባለውን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እንቲንቢንያነ እንቲንቢንያነን አላስገረመም።

«ይህ እኛን የሚያስገርም ጉዳይ አይደለም፣ ምክንያቱም ኢያን ካማ፤ እ ጎ አ በ 2008 ፕሬዚዳንት ከሆኑበት ጊዜ አንስቶ አeንድም ቀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው አያውቁምና! ነው። በፍጹም አይፈልጉም! በግልጽ እንደተናገሩትም፣ የግሉን ፕረስ አይወዱትም። ሐሳብን በሐሳብ መግጠም ፣መከራከር አይወዱም»።

ኤድጋር ሲማኔ የተባለው የአንድ ጋዜጣ ዘጋቢ እንዲያውም በደቡብ አፍሪቃ ቴሌቭዥን በኩል የቦትስዋና መሪዎች ባልተጨበጠ ነገር የሚሠጉ፣ ተፎካካሪዎቻቸውን በስለላ ድርጅት በኩል መቅኖ ለማሳጣት የሚሞክሩ ናቸው ነው ያለው።

«መንግሥት ፤ ዐበይት የሆኑ ጉዳዮችን በማንሳት እንዳንጽፍ ለማፈን በመጣር ላይ ነው የሚገኘው። ፍርድ ቤት የያዘው አንድ ጉዳይ አለ። ስለዚህ፤ ስለሙስና እንዳንጽፍ መንግሥት ለማገድ ነው የሚጥረው። የሥለላው መ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሰፊው በሙስና የተዘፈቁ ስለመሆናቸው ብዙ የተነገረ አለ። መንግሥት አጣርቶ ለጉዳዩ እልባት እንዲደረግለት በፍጹም የወሰደው አንዳች ርምጃ የለም።»

የጎረቤት ዝምባባዌን መሪ ሮበርት ሙጋቤን ሰብአዊ መብት አያያዝ አጥብቀው የሚነቅፉት የቦትስዋናው ኢያን ካማ፤ በአገራቸው ሁሌ ጥሩ ተምሳሌት ሆነው አልተገኙም።የተቃውሞ ፖለቲከኞች እንዲያውም የስለላው መ/ቤት ያዋክበናል። የኃይል ርምጃ የወሰደበት ጊዜም አለ። ሴቶች፤ ነባር ልማድ በሚል ፈሊጥ አድልዎ ይፈጸምባቸዋል።የ«ሳን» ብሔረሰብ (የቁጥቋጦ ሰዎች የሚባሉት) ይገፋሉ። ሶዶማዊነት ያስቀጣል። ሙት በቃ ብያኔ አሁን ድረስ ተፋጻሚነት አለው። ጋዜጠኛ ኤድጋር ሲማኔ እንደሚለው፣ ቦትስዋና ባለፉት ዓመታት ፤ ቀስ በቀስ ወደ አምባገነንነት እያመራች ነው።

«ጉዳዩ ቀስ በቀስ ሲፈጸም የቆየ ነው። አሁን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ፈጥጦ እየታየ ነው። በሀገሪቱ ፤ ከሕግ ውጭ ፣ በዘፈቀደ ፣ ሰዎች ስለመገደላቸው ተናግረናል። አንድ ንዑስ ወንጀል የፈጸመ ሰው በምሥጢራዊው ወታደራዊ ኃይል በ 10 ጥይት ነው የተገደለው። እንዴት አንድን ሰው ሕግ ፊት ሳያቀርቡ ግድያ ይፈጸማል? ተጠርጣሪውን ፖሊስ አልያዘውም። በቀጥታ ነው የተገደለው።»

ቦትስዋና ፤ በኤኮኖሚ ረገድም ቢሆን ሳንክ አላጋጠማትም አይባልም ። በአልማዝ ማዕድን ማዕድኑ ሽያጭ የተመካው ምጣኔ ሀብት ፤ ቀደም ባሉት ጊዜያት እንደታየው ፈጣን ዕድገት አላመጣም። ከየ 5ቱ ቦስዋናዊ አንዱ ከድህነት ጠርዝ በታች ነው የኑሮ ደረጃው!

የሥራ አጦች መጠን በይፋ እንደሚገለጸው ከሆነ 18 ከመቶ ነው። በወጣት ቦስዋናውያን ዘንድ ደግሞ ከተጠቀሰው ቢልቅ እንጂ አያንስም። መሬት ማከፋፈሉ ተግባር አልተካሄደም፤

Wahlen Botsuana 2009

150,000 የሚሆኑ ዜጎች እናገኛለን ብለው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ባለፉት ወራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋጋ መናርም ጋራ እንዳጋባ ነው።

ቦትስዋና ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ተላቃ እ ጎ አ በ 1966 ነጻነት ካወጀችበት ጊዜ አንስቶ ፣ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ በሰፊ ብልጫ ነበረ ምርጫ የሚያሸንፈው።

አሁን ግን ፍጹም አብላጫ ድምጽ ማግኘት መቻሉ አጠራጥሯል። ጥያቄው አሁን፣ የተቃውሞው ወገን ምን ያህል ውጤት ያስመዘግብ ይሆን ? የሚለው ነው።

ተክሌ የኋላ/ያን ፊሊፕ ሹዑልተር

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic