የቦምብ ጥቃት በነቀምት | ኢትዮጵያ | DW | 13.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቦምብ ጥቃት በነቀምት

ትናንት በነቀምት ከተማ የደረሰ የቦምብ ጥቃት በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ጥቃት የደረሰበት ሆቴል ባለንብረቶች ለዶይቼ ቬለ DW ገለፁ። ከሰሞኑ  በነቀምት የቦምብ ጥቃት ሲደርስ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:48

በጥቃቱ የሞቱም የተጎዱም አሉ

 የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ከስምንት ወራት በፊት የተቋቋመው የምዕራብ ኢትዮጵያ የእዝ ጣቢያ ማለትም ኮማንድ ፖስት ሥራ ላይ በሚገኝበት በዚህም ወቅት በዚህ አካባቢ ግጭት እና የሰው ሕይወት መጥፋቱ ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን የአሶሳው ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ በመጥቀስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic