የብዝሃ ህይወት ጉባኤ እና የኢትዮጽያ ቡና | ባህል | DW | 10.06.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የብዝሃ ህይወት ጉባኤ እና የኢትዮጽያ ቡና

በቦን ከተማ ለሶስት ሳምንት የተካሄደዉና የአለም ህዝብን ያሰባሰበዉ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ የተለያዩ አገር ህዝቦች ባህላቸዉን፣ አገራቸዉን ያስተዋወቁበት መድረክ ነበር። በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ በርካታ ኢትዮጽያዉያን ተካፋይ ነበሩ።

default

የኢትዮጽያ ቡና በቦኑ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ

የራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት ቦን ከተማ ከአለም የተሰባሰቡ የከባቢ አየር ጥበቃ አዋቂዎች፣ የተለያዩ አለማቀፍ የግብርና ድርጅቶች፣ የመንግስት ባለ ስልጣናት እና፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ። በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ በርካታ ኢትዮጽያዉያን ተካፋይ ነበሩ። በጉባኤዉ የኢትዮጽያ ባህላዊ አልባሳትን ያደረጉ ወጣቶች ያገራችንን ባህላዊ የቡና አፈላል ስርአት የቡና አቆላሉን የቡና ቁርሱን እጣኑን ረከቦቱን እና ጉዝጓዙን አቅርበዉ፣ ባህላቸዉን የአገርን ባህልን ሲያስተዋዉቁ ሰንብተዋል።ከጉባኤዉ አዳራሽ አጠገብ ከተለያዩ አገራት የመጡ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የአካባቢ ጥበቃን በማስመልከት ለአለም ህዝብ ለማሳየት ያቀረቡትን የተለያዩ ንድፈ ሃሳቦች ለተመልካች ያቀርባሉ።

Die Bonner Oberbürgermeisterin Bärbel Dieckmann auf äthiopische Kaffeezeremonie in Bonner Konferenz der biologischen Artenvielfalt

የቦን ከንቲባ ቤርብል ዲክማን በቡና አፈላሉ ስነ-ስርአት ላይ አንዷ እንግዳ ነበሩ

የብዛሃ ህይወት ወይም የባዮ ዳይቨርሲቲ ባንክ እንደሆነች የሚነገርላት አፍሪቃችንን ለመጠበቅ ጉባኤዉ በርካታ ርዕሶችን ዳስዋል። በዘንድሮዉ የቦን ጉባኤ የቡና መገኛ በሆነችዉ ኢትዮጽያችን ዉስጥ በተለይ በወፍ ዘራሽ የሚበቅለዉን የቡና ዝርያ ለመጠበቅ ከፍተኛ ምርምር እና እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑን በቦን ዩንቨርስቲ ዉስጥ የብዝሃ ህይወት አዋቂዎች እና ኢትዮጽያዉያን ምሁራን ገልጸዋል። ከዚህ ባሻገር የቡና አፈላል ስርአታችንን ከባህላዊ አለባሶቻችን ጋር ለሶስት ሳምንት ለህዝብ ቀርቦአል። የዝግጅት ክፍላችን በቡና ግብዣዉ ጥሪ ደርሶት ወደ ጥሪዉ ቦታ መቅረጸ ድምጻችን ይዘን ቢና ለመጠጣት ሄድን። ቡናዉ የሚፈላበት አዳራሽ በግምት አምስት መቶ ሜትር ስፋት አለዉ። በአዳራሹ ዉስጥ ከተለያዩ አገር የመጡ ህዝቦች በመኖራቸዉ ኢትዮጽያዉያንን ለማግኘት ትንሽ ቆም ብዩ ወደ ግራ ወደ ቀኝ ተመለካክተን ወደ አዳራሹ ገባ ስል የእጣኑ መአዛ ሸተተት አለን እና በርግጥ በገባትነት አዳራሽ ዉስጥ መሆኑን አራጋግጠን ወደ ፊት አይናችን ወርወር በማድረግ ፍለጋችንን ቀጠልን፣ እየተቃረብን ስመጣ የቡናዉ ጭስ ቦልቦል ሲል ታየን ጠጋ ስል በሰፊዉ ህዝብ ተሰብስቦ ቆምዋል የቡናዉ ጭስ ከላይ ቦልቦል ይላል። የከበበዉን ህዝብ እንደምንም ፈልቀቅ አድርገን ገባን፣ ሁለት ወጣት ሴቶች ናቸዉ የወሎ ጥበብ ቀሚሳቸዉን አድርገዉ ልዩ አሸንክታባቸዉን አጥልቀዉ ጉድ ጉድ ይላሉ። አንድኛዋ በጀበና የፈላችዉን ቡና ትቀዳለች፣ አንድኛዋ ደግሞ የቡና ቁርስና በሲኒ የተቀዳዉን ቡና ለህዝብ ታድላለች። የከሰል ምድጃዉ የሸክላ ድስቱ ቡና ቁርሱ የቡና ሙቀጫዉ ቀራርቦአል።

Teilnehmer aus Süd Amerika in Bonner Konferenz der biologischen Artenvielfalt verkosten äthiopischen Kaffee

ከደቡብ አሜሪካ የመጡ የጉባኤዉ ተሳታፊዎች የኢትዮጽያን ልዩ ቡና ቀምሰዋል

እጣኑ አልበዛም እንዴ ! ስንል ጠየቅን አይ ፈረንጆቹ ወደ ዉታል! ግን ትናንትና የቡና ጭሱን አይተዉ እሳት የተነሳ መስሎአቸዉ ፖሊሶች ተንጋግተዉ መጥተዉ ነበር። የጭሱ ሽታ ጣፍጦ ሲያገኙት ረጋ ብለዉ ቆሙ ከዝያም የኢትዮጽያ ቡና አፈላል ስርአት ነዉ እንኩ የቡና ቁርስ ያዙ ብለን ቆሎና ቂጣ ሰጠናቸዉ አለች ቡና የምታፈላዉ ልጅ፣ በመቀጠል ቂጣዉ እንዴት እንደሚበላ ባላሳያቸዉም ቆሉዉን አንድ ጥሪ እያነሱ ስላስቸገሩኝ ባገራችን እንዲህ ነዉ የሚዘገነዉ እያልኩ በእጄ አፈስ አድርጌ እንዴት እንደሚቃም ሁሉ አሳየኻቸዉ ስትል በፈገግታ አወጋችን ከዝያማ በርኩማ ተሰጥቶን በክብር ቡናችንን መጠጣት ያዝን!
የኢትዮጽያ ቡና በመኖሩን ሰምቼ የኢትዮጽያ ፍቅር ስላለኝ ነዉ የመጣሁት ያለችን ጀረመናዊት ወጣት የደን ጥበቃ ትምህርቷን ለማጠናቀቅ በኢትዮጽያ በቦንጋ ዉስጥ ለሁለት አመት በመኖርዋ አማረኛዉን አቀላጥፋ ባትናገርም አትታማም፣ የባህል መድረካችን በቡናዉን ግብዣ ተገኝቶ እድምተኞችን አነጋግሮአል ያድምጡ