የብራዚል ተቃዉሞ | ዓለም | DW | 24.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የብራዚል ተቃዉሞ

ቀጣዩን የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ አስተናጋጅ አገር ብራዚል ባልተጠበቀ የተቃዉሞ ሰልፍ እየተናጠች ነዉ።

በእግር ኳስ አድናቂና ወዳድነቱ የሚታወቀዉ የብራዚል ሕዝብ ለዓለም ዓቀፉ ጨዋታ ዝግጅት የሚገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ስታዲዮሞች ለመሠረታዊ መብቱ የሚያቀርበዉን ጥያቄ እንዳጋጋሉት ነዉ የሚገመተዉ። ሃኪም ቤቶችና ትምህርት ቤቶችም እንዲገነቡ የሚሉት የተቃዋሚ ሰልፈኞች ጥያቄ የመንግስታቸዉም ጥያቄ መሆኑን በመግለጽ የሕዝብን ቁጣ ለማብረድ የሚሞክሩት ፕሬዝደንት ዲላማ ሩሴፍ ዛሬ የተቃዉሞዉን መሪዎች ለማነጋገር ቀጠሮ መያዛቸዉ ተሰምቷል። ፕሬዝደንቷ ዓርብ ዕለት በቴሌቪዝን ለመላዉ የአገሪቱ ሕዝብ ባሰሙት ንግግርም ሙስናን ተዋጉ ለሕዝቡ የሚቀርቡ አገልግሎቶች ይሻሻሉ ለሚለዉ የጎዳና ላይ የተቃዉሞ ጥሪ ጆሮ እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እጅግም የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በማይታይባት ብራዚል ወደ1,2 ሚሊዮን ሕዝብ አደባባዊ መዉጣቱ የአገሪቱን የፖለቲካ መሪዎች ከእንቅልፍ ያባነነ መስሏል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል የሰሞኑን የብራዚሊያዉያንን የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በአጭሩ ቃኝቶታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic