የብራስልሱ ጉባኤ በጀርመኖች ዓይን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የብራስልሱ ጉባኤ በጀርመኖች ዓይን

ቱርክ ከግሪክ የሚጠረዙ ስደተኞችን እድትቀበል፤ ዜጎችዋ ያለ ቪዛ አዉሮጳ እንዲገቡ እና ለአዉሮጳ ሕብረት አባል ትሆን ዘንድ ድርድር እንዲጀመር ያቀረበችዉን ጥያቄ ሕብረቱ ከተቀበለዉ ለጀርመን ፖለቲከኞች ሌላ የዉዝግብ ርዕስ መሆኑ አይቀርም

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:17 ደቂቃ

የብራስልሱ ጉባኤ በጀርመኖች ዓይን

የጀርመን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ተንታኞች የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት እና የቱርክ መሪዎች ብራስልስ ዉስጥ የሚያደርጉትን ድርድር ዉጤት በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተሉት ነዉ።ድርድሩ አግባቢ ሥምምነት ላይ ከደረሰ የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስደተኞችን በመቀበላቸዉ ከራሳቸዉ ፓርቲ ባለሥልጣንት የሚሰነዘርባቸዉን ተቃዉሞና ትችት በመጠኑም ቢሆን ይቀንስላቸዋል ነዉ የሚባለዉ።ያም ሆኖ ቱርክ ከግሪክ የሚጠረዙ ስደተኞችን እድትቀበል፤ ዜጎችዋ ያለ ቪዛ አዉሮጳ እንዲገቡ እና ለአዉሮጳ ሕብረት አባል ትሆን ዘንድ ድርድር እንዲጀመር ያቀረበችዉን ጥያቄ ሕብረቱ ከተቀበለዉ ለጀርመን ፖለቲከኞች ሌላ የዉዝግብ ርዕስ መሆኑ አይቀርም።የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ስቱዱዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሩዋለሁ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic