የብሪታንያ ፈንድ ለጨቋኝ መንግሥታት | ኢትዮጵያ | DW | 06.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የብሪታንያ ፈንድ ለጨቋኝ መንግሥታት

ከአራት ዓመት በፊት ታላቅዋ ብሪታንያ በኢትዮጵያ-ሶማሌ ክልል ወይም በኦጋዴን ከ10 ሺሕ እስከ የሚደርሱ 14,000 የልዩ ፖሊስ ባልደረቦችን ለማስልጠን ከ13 እስከ 15 ሚሊዮን ፓዉንድ እገዛ ማድረጓን ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:22

ጨቋኝ መንግሥታት

ልዩ ፖሊሶች የሰለጠኑትበአከባብዉ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ነው ተብሎ ቢነገርም፣ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በራሳቸዉ ማህበረሰብ ላይ ማድረሳቸዉን ዘገባዎች ይጠቅሳሉ። ልዩ ፖሊስ፤ በቅርብ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ-ሶማል ክልል አዋሳኝ ድንበሮች  ሺዎች ለመፈናቀላቸዉ እና መቶዎች ለመገደላቸዉ ተጠያቂ ነዉ ተብሎ ይወቀሳል።
ልዩ ፖሊስ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የይፈፅማል የሚባለዉን በደል ታላቅዋ ብሪታንያ ብታዉቅም አሁንም ርዳታ ከማድረግ አልተቆጠበችም።

በትላንትናዉ እለት ለፍትሕ መከበር የሚታገለዉ ተቋም፣ ግሎባል ጃስትስ ናዉ የተሰኘዉ፣ ባወጣዉ ዘገበም  የብሪታንያ መንግስት የሚትሰጠዉ ገንዘብ ሰላማዊ ሰዎችን ለመጨቆኚያ እየዋለ መሆኑን አጋልጧል።የብሪታንያ የግጭት፣ መረጋጋትና ደሕንነት ፈንድ  በፀጥታ አስተዳደር ወይም security managment ላይ በድሕረ-ምረቃ ለማስልጠን እንዲሁም የሰለም ማስልጠኛ ተቋማትን ለመርዳት ለኢትዮጵያ መንግስት ከአንድ ሚሊዮን ፓዉንድ ወይም ከ36 ምልዮን ብር በላይ እንደሰጠ ዘገባዉ ይጦቁማል።

የግሎባል ጃስትስ ናዉ ዳይሬክቴር የሆኑት ኒክ ዲርራደን እንዲሕ አይነት መረጃ ምስጥራዊ በመሆኑ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ እንደነበረ ይናገራል፣ «አንዱ ትልቁ መሰናክል የሆነብን የፋንዱ ጉዳይ በጣም ምስጥራዊ በመሆኑ ነዉ። ይህን በጠና መልክ ነዉ የምናየዉ። ምክንያቱም በገንዘቡ አዉንታዊ ነገር መስራት ብትፈለግም የመከላክያና የደሕንነት ሃይሎች በሰበዓዊ መብት ጥሰት ዉስጥ ከተሳተፉና ፈንዱ ግልጽነት ከጎደለዉ የገንዘብ ርዳታዉ ማሕበረሰቡን ሕይወት የሚያሻሽል ሳይሆን ጨቋኝ መንግሥታት በሕዝቡ ላይ ያላቸውን ጉልበት ለማጠናከር ይሆናል።»

ኒክ ዲርራደን እንደሚሉት የርዳታ ዓላማ ድሕነትን ለማጥፋትና ማህበረሰቡን ለማገዝ ነዉ። ታላቅዋ ብሪታንያ ግን ርዳታዉን ያዋለችዉ የራስዋን ጥቅም ማሟያና ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ኢራቅ፣ በርማ፣ ባህሬን ያሉ ጨቋኝ መንግሥታትን ጉለበት ማጠናከርያ መሆኑን ነዉ። ይህም የታላቅዋ ብሪታንያ ተቃዋሚ ፓርትዎች መንግስት  መልስ እንድሰጥ እየጠየቁ እንድምገኙ ኒክ ይናገራል፣ «በርግጥ አሁን የተቃዋሚዉ ፓርቲ መሪ  ጄረሚ ኮርቢን ዘገባችን ያጋለጠዉን ጉዳይ አስመልክተዉ ለጠቅላይ ምንስትሯ ቴሬሳ ሜይ ድብዳቤ ፅፎዉላቸዋል። እኛም ሜይ ምን እንደሚሉ በጉጉት እየጠበቀን እንገኛለን።»

የብሪታንያ ርዳታ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ጠቅሟል ስንል የዋትስአፕ ተከታታዮቻችን ጠይቀን ነበር። በፌስቡክ  ከተከታተሉት ደግሞ ስምዖን ሩፋኤል የተባለዉ «ዙሮ ዙሮ ገንዘቡ ከውጭ ካልተገኘ ከኛው ሀብት መመዝበሩ የማይቀር በመሆኑ የኛውን ሀብት ከመመዝበር በማዳን መልኩ ይጠቅመናል» ሲል ሚካኤል ቴድ የተባለ ደግሞ «የኢትዮጵያ ህዝብ እንኩዋን በእርዳታ ገንዘብ ሊጠቀም እግዜር የሰጠውን ነፃነትም አላገኘም፣ እሱንም ተቀምቶ ባዶውን የህልም ህይወት እየገፋ ነው» ሲል አስተያየታቸዉን ፅፎሊናል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ  
 

Audios and videos on the topic