የብሪታንያ ስንብት እና ፎን ዴር ላየን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 04.02.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የብሪታንያ ስንብት እና ፎን ዴር ላየን

ምንም እንኳን ብሪታንያ ባለፈው ሳምንት አርብ ለሊት ከህብረቱ አባልነት ብትወጣም ሙሉ በሙሉ ከህብረቱ አልተላቀቀችም።በ11 ወሩ የሽግግር ጊዜ ሁለቱ ወገኖች በወደፊቱ ግንኙነቶቻቸው ላይ ድርድሮች ያካሂዳሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 07:55

የብሪታንያ ከህብረቱ መዉጣትና የኮሚሽን ፕሬዝዳንቷ

ብሪታንያ ከ4 ቀናት በፊት በጎርጎሮሳዊው ጥር 31 2020 ከአውሮጳ ህብረት አባልነት በይፋ ወጥታለች። ብሪታንያ ከ47 ዓመታት በኋላ የአውሮጳ ህብረትን ለቃ መውጣቷ የተለያዩ ስሜቶችን ፈጥሯል። ከሁለት ወር በፊት የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንትነትን የተረከቡት ኡርሱላ ፎን ዴር ላየን የብሪታንያን ከህብረቱ አባልነት መውጣት ከቤተሰብ አባላት አንዱ ለመለየት ሲወስን ሁሌም አሳዛኝ መሆኑን በመጥቀስ ነበር ምን እንደተሰማቸው በዋዜማው ለዶቼቬለ የገለጹት 
«ብሪታንያ በጣም ብዙ ጓደኞች አሉኝ።ለአንድ ዓመት በለንደን ኦፍ ኤኮኖሚክስ ተምሬያለሁ።ብሪታንያ ዘመዶችም አሉኝ።ከልጆቼ ብሪታንያ የተማሩ አሉ።እናም ብዙ የሚያስተሳስሩ ጉዳዮች ስላሉ ስሜታዊ ቀን ነው።»

ብሪታንያ በመውጣትዋ ምን ቅር ይልዎታል?
የተግባር ሰው መሆናቸውን አይረሳኝም።ይህ በጣም አግዟል።አንድን ነገር መጨረሻ ሳያደርሱ አይተዉም።የብሪታንያውያን እጹብ ድንቅ የቀልድ ለዛም እንዲሁ ውል ይለኛል።በሌላ በኩል ከነገ ጀምሮ ከብሪታንያ ጋር የምንነጋገረው እንደ ሦስተኛ ወገን ነው።»

የብሪታንያ ህዝብ ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት አባልነት እንድትወጣ ከወሰነ ከሦስት ዓመት በኋላ ብሬግዚት እውን ሆኗል።የአውሮጳ ህብረት እና ብሪታንያ በብሬግዚት ውል ላይ ከመስማማታቸው በፊት ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፈዋል። ምንም እንኳን ብሪታንያ ባለፈው ሳምንት አርብ ለሊት ከህብረቱ አባልነት ብትወጣም ሙሉ በሙሉ ከህብረቱ አልተላቀቀችም። በ11 ወሩ የሽግግር ጊዜ ሁለቱ ወገኖች በወደፊቱ ግንኙነቶቻቸው ላይ ድርድሮች ያካሂዳሉ። አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ከብሪታንያ ጋር በመለያየቱ ሂደት ከባዱ ጊዜ አሁን ነው የሚጀምረው ይላሉ እርስዎ በዚህ ይስማማሉ?ዶቼቬለ ለፎንዴር ላየን ያቀረበው ሌላ ጥያቄ ነበር።

«ከባድ፣ፍትሃዊ እና ፈጣን ድርድሮች ነው የሚሆኑት።ብሪታንያ አሁን ሦስተኛ ሀገር መሆን ስለመረጠች ምን ያህል ለወጡ ገበያ ቅርብ መሆን ይፈልጋሉ የሚለውን ማወቅ አለብን።መቅረብ በፈለጉ ቁጥር ለወጡ «ገበያ የጋራ ደንቦች» ተገዥ መሆን አለባቸው።ራሳቸውን ካራቁ በወጡ ገበያ መሳተፋቸው አስቸጋሪ ይሆናል።ከቀረቡ ግን ይህ ይቀየራል ስለዚህ ከሞላ ጎደል ምርጫው የነርሱ ነው።» 


የ11 ወራቱ የብሬግዚት የሽግግር ጊዜ ምንም ይሁን ምን እንደማይገፋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተናግረዋል። ያ ማለት ደግሞ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ብሪታንያ ያለ አንዳች ውል ከህብረቱ ትወጣለች ማለት ነው ።ይህ ጠቃሚ የፖለቲካ አካሄድ ነው ብለው ያስባሉ? 
«ይህ የርሳቸው ውሳኔ ነው።ግን በዓመቱ ማብቂያ ውሳኔያቸው ይህ ከሆነ እኛ በደንብ ተዘጋጅተናል።ምክንያቱም ለኛ በመውጫው ስምምነት ላይ እጅግ አስቸጋሪ የነበሩት የውሉ ክፍሎች መፍትሄ አግኝተዋል።የዜጎች መብቶች የፋይናንስ እና የአየርላንድ ጉዳይን አሳክተናል።በዚህ ምንም ቅሬታ የለንም።አሁን እኛ ለመጪው ድርድር በጣም ጠንካራ አቋም ላይ ነው የምንገኘው።ብሪታንያ ከእቃዎቿ ግማሽ ያህሉን የምትልከው ወደ አውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ነው።  በዓመቱ መጨረሻ ብሪታንያ ያለ ስምምነት የምትወጣ ከሆነ ከባድ ነው የሚሆነው።እኛ እንደ አውሮጳ ህብረት የምናደርገው በበጋ ወራት ምን ላይ እንደምንገኝ ካየን በኋላ እንወስናለን።ያም ሆኖ በዓመቱ መጨረሻ ስምምነት ላይ ባንደርስ አዎ ብሪታንያ ያለ ስምምነት ትወጣለች።ሆኖም ድርድሮቹ መቀጠል ይችላሉ።»


ከብሪታንያ ጋር በነጻ ንግድ ውል ላይ እንደራደራለን ወይም ለመደራደር እንሞክራለን ብለዋል።በነጻ ንግድ ስምምነት ላይ ለመደራደር በእርግጠኝነት አንድ ዓመት በቂ አይደለም ይላሉ?


«የነጻ ንግድ ስምምነት ብቻ አይደለም።ቢያንስ ስ 10 ወይም 11 የተለያዩ ፋይሎች እና ርዕሰ ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ የጸጥታ ጉዳይ ለስለዚህ በርካታ የመደራደሪያ ጉዳዮች ስላሉ 7 ቀናት እና 24 ሰዓታት እንሰራለን።ከዚያም ድርድሩ እንዴት ወደፊት እንደሚራመድ እናያለን።»


በመደበኛ ሁኔታዎች እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች በአጭር ጊዜ ድርድር ተካሂዶባቸው አያውቅም ይላሉ?


«ከመነሻዬ እንዳልኩት እኔ እንደማስበው ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገናል።ሆኖም ለዚህ ውሳኔ ሁለት ወገኖች ያስፈልጋሉ።እናም እንዳልኩት እኛ አሁን ጥሩ አቋም ላይ ስላለን ስለዚህ ጥያቄ ላይ ብዙም አንጨነቅም።»  
ቦሪስ ጆንሰን የሽግግሩ ጊዜ አይገፋም ፣ እምቢ ካሉ ብሪታንያ ያለ ስምምነት ህብረቱን ለቃ መውጣትዋ የማይቀር ነው ይላሉ?


«ድርድሮቹን አሁን መጀመር አለብን ብዬ አስባለሁ።ምክንያቱም ብሪታንያ ስለሚኖራት ሃላፊነት አሁን ማወቅ ስላለብን።እኛም የራሳችን ሃላፊነት አለብን።ነገር ግን በዓመቱ መጨረሻ ላይ የሚሆነውን አሁን መተንበይ ጥሩ ነው ብዬ አላስብም በድርድሩ ሂደት ሊኖሩ ይችላሉ ብዬ ያሰብኳቸውን አማራጮች አዘጋጅቻለሁ  ይሁን እና አሁኑኑ ድርድሮቹን እንጀምር።»


በእነዚህ ድርድሮች የርስዎ ዋና ግብ ምንድን ነው? 


«ዋናው ዓላማዬ ከብሪታንያ ወዳጆቻችን ጋር ጥሩ ትክክለኛ እና ከሌሎች ሁሉ የቀረበ አጋርነት መመስረት ነው። የምንጋራቸው በርካታ ጥቅሞች አሉ።ወጡን ገበያችንን መጠበቅ የምንደደራደርበትን ሁኔታ  መጠበቅ።ከብሪታንያ ወዳጆቻችን ጋር የመደራደሪያ መድረክ ማመቻቸት ህብረቱ አንድ አቆም ይዞ መቀጠሉን ማረጋገጥ ናቸው።» 
ወደፊት የዛሬ 10 ዓመት አሻግረው ሲመለከቱ ብሪታንያ ወደ አውሮጳ ህብረት ለመመለስ የምትፈልግ ይመስልዎታል። 
ይህ የነርሱ ስራ መሆን እንዳለበት ሁሌም ለልጆቼ እነግራቸዋለሁ።ይህ የብሪታንያ ህዝብ ጉዳይ ነው።ለኔ ግን ማለት ያለብኝ አስፈላጊ ጉዳይ አለ።«እኛ ወዶጆች ነን።»የወደፊት በአጋርነታችን እንቀጥላለን።»የዓየር ንብረት ለውጥን መቋቋም ወይም ዲጂታላዜሽንን የመሳሰሉ በርካታ የጋራ ጉዳዮች አሉን።አንድ ላይ መሥራት በሚገባን በአንድ መስመር ላይ ነው ያለነው።የዚህን በጎ ጎን እንመልከት ከዚህም የተሻለውን ደግሞ ተግባራዊ እናድርግ።


ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች