1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ ርዳታ ለኢትዮጵያና አጠቃቀሙ

ረቡዕ፣ ሰኔ 29 2003

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎችና የመብት ተሟጋቾች የኢትዮጵያ መንግሥት በርዳታ የሚያገኘዉን ገንዘብ ለገዢዉ ፓርቲ አገልግሎት ያዉለዋል በማለት ይወቅሳሉ

https://p.dw.com/p/RXwg
ኢትዮጵያ-ከሁለት ዓመት በፊትም ረሐብ ነበርምስል picture-alliance/dpa

የብሪታንያ መንግሥት ለረሐብ ለተጋለጡ ኢትዮጵያዉያን መርጃ በቅርቡ የሰጠዉ ገንዘብ ለተረጂዉ ሕዝብ መድረሱን የሚቆጣጠርበት ሥልት መቀየሱን አስታወቁ።የብሪታንያዉ የልማትና ተረድኦ ሚንስትር አንድሩ ሚሼል በቅርቡ እንዳስታወቁት ሐገራቸዉ ለረሐብ ለተጋለጠዉ 1.3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ መርጃ 38 ሚሊዮን ፓዉንድ ወይም 61 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሠጥታለች።የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎችና የመብት ተሟጋቾች የኢትዮጵያ መንግሥት በርዳታ የሚያገኘዉን ገንዘብ ለገዢዉ ፓርቲ አገልግሎት ያዉለዋል በማለት ይወቅሳሉ።የብሪታንያዉ የልማትና ተራድኦ ምክትል ሚንስትር ስቴፋን ኦ ብሬይን ለለንደኑ ወኪላችን ለድልነሳ ጌታነሕ እንደነገሩት ግን ርዳታዉ ከታሰበለት አላማ ዉጪ አይዉልም።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ