የብሪታንያ ርዳታና የሰብአዊ መብት አያያዝ በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 18.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የብሪታንያ ርዳታና የሰብአዊ መብት አያያዝ በኢትዮጵያ

ለኢትዮጵያ ፣ በሰፊው የልማት ርዳታ ከሚሰጡ አገሮች አንዱ የብሪታንያ መንግሥት ሲሆን፤ ለሰብአዊ መብት ጥሰት ግን ደንታ የለውም እያሉ የሚወቅሱት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥቂቶች አይደሉም። ከጋምቤላ ፣ አንድ ያመረሩ ኢትዮጵያዊ አርሶ

አደር ፤ በብሪታንያው የልማት ርዳታ ሰጪ ድርጅት (DFID)ትብብር ፣ የሠፈራ መርኀ ግብር በተባለ ርምጃ ርስት ጉልቴን ተነጥቄ ለስደት ተዳርጌአለሁ ሲሉ በጠበቆቻቸው በኩል የብሪታንያን መንግሥት ከሰው ነበር። በለንደን አንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፣ ለብሪታንያ መንግሥትና ለሌሎችም የማስጠንቀቂያ ምልክት ሳይሆን አይቀርም የተባለ ብይን ሰጥቷል። ተክሌ የኋላ የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (HRW) የአፍሪቃ ክፍል ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ሲሆን፤ በዚያች ሃገር ለሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት ግን ደንታ የለውም እያሉ የሚወቅሱት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥቂቶች አይደሉም።

ከጋምቤላ እንዲያውም አንድ ያመረሩ ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር ፤ በብሪታንያው የልማት ርዳታ ሰጪ ድርጅት ትብብር ፣ የሠፈራ መርኀ ግብር በተባለ ርምጃ ርስት ጉልቴን ተነጥቄ ባዶ እጄን ቀርቼ ለሥቃይና ለመከራ፣ እንዲሁም ለስደት ተዳርጌአለሁ ሲሉ በጠበቆቻቸው በኩል የብሪታንያን መንግሥት ማስከሠሳቸውና በለንደን ከአንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለብሪታንያ መንግሥትና ለሌሎችም የማስጠንቀቂያ ምልክት ያለው ብይን ማስገኘታቸው ታውቋል። ተክሌ የኋላ የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (HRW) የአፍሪቃ ክፍል ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

Kleinbauern in Äthiopien Äthiopien, Biospritproduktion, Landraub, Nahrungsmittelkrise, Nothilfe

በለንደን አንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፤ የብሪታንያው ዓለም አቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት (UK DFID) ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከተለውን የሰብአዊ መብት አያያዝም ሆነ መመሪያውን መለስ ብሎ እንዲመረምርና እንዲያስተካከል ባለፈው ሰሞን ብይን ማስተላለፉ ታውቋል። ይህ ለብሪታንያ ና ለተለያዩ ለጋሽ ለሚሰኙ መንግሥታት ለድርጅቶችም የሚያካፍለው ትምህርት ምን ይሆን?

የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (HRW) የአፍሪቃ ክፍል ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ ሚስ ሌስሊ ሌፍኮቭ---

«ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል፣ (DIFID) የሰብአዊ መብት መርኅን አክብሮ እንዲይዝ ተሟጋች ያጋጠመው። ድርጅቱ፤ የልማት ርዳታ በሚያቀርብበት ቦታ ፣ ሰብአዊ መብት አለመጣሱን እንዲያረጋግጥ፣ የተፈተነበት ሁኔታ ኢትዮጵያን የሚመለከት ነው። እዚህ ላይ አንደ የጋምቤላ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ፣ እንዳሉት ድርጅቱ ፣ በጋምቤላ፣ በሠፈራ መርኀ ግብር ሥም ሰብአዊ መብት እንደሚረገጥ በአግባቡ አልመረመረም። ስለሆነም ርዳታው ለሰብአዊ መብት ረገጣ ነው የዋለው በማለት ነው የከሰሱት። እናም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህ ጉዳይ ፤ ይህ ወቀሳ፣ ሙሉ-በሙሉ ሕጋዊ ምርመራ እንዲካሄድ የሚያስችል መሆኑን ነው የበየነው። ይህ ጠቀሚ የሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ርምጃ ሲሆን፤ ጉዳዩ ረጅም ሒደት ያለው ነውና ድርጅቱ፤ የራሱን የሰብአዊ መብት መርሕ አክብሯል ? ጥሷል? --እንደሚመረመር የሚያደርግ ነው።»

Saatgut in Äthiopien , Biospritproduktion, Landraub, Nahrungsmittelkrise, Nothilfe

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ስለመኖሩ ሲነገር ረጅም ጊዜ ነው። ይሁንና አንዳንድ መንግሥታትና ድርጅቶች ፤ ይኸው የብሪታንያ መንግሥት የልማት ርዳታ ድርጅት ጭምር ዐይተው እንዳላዩ ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ ይሆናሉ የሚል ወቀሣ ሲሰነዘርባቸው ነው የሚሰማው ፤ የተጠቀሱት የጋምቤላ ተወላጅ በሠነዘሩት ክስ ብቻ አይደለም። ከተለያዩ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የሚቀርቡ ስሞታዎች አሉና! ግን ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የልማት ርዳታ ይሰጣሉ የሚባሉ መንግሥታት ለምንድን ነው ዝምታን የሚመርጡት?

«እንደሚመስለኝ በኢትዮጵያ ላይ ለሚከተሉት አመራር ዘይቤ ፣ በዛ ያሉ ምክንያቶች ሳይኖሯቸው አልቀሩም። እርግጥ ነው ኢትዮጵያ ለብሪታንያና ሌሎችም መንግሥታት በልማት ረገድ እጅግ ጠቀሚ ተጓዳኝ ናት፤ በዓለም ውስጥ፣ የልማት ርዳታ በገፍ ከሚያገኙ አገሮች አንዷ ናት። ኢትዮጵያ ፣ በያመቱ 4 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ የምታገኝ ሀገር ናት ፤ ሌሎች ጉዳዮችም አሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ለብዙ ምዕራባውያን መንግሥታት ጠቃሚ የፀጥታ ጥበቃ ጉዳይ ተባባሪ ፣ ተጓዳኝ ነው። ይኽም ባካባቢው የፀረ-ሽብር ዘመቻን የሚያካትት ነው። ምንም እንኳ የሰብአዊ መብት ይዞታ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ ቢገኝም እንደሚመስለኝ ያን መንግሥት በይፋ መገሠፅ አይፈልጉም።»

የጋምቤላው ተወላጅ የሠፈራ መርኀ ግብርን በተመለከተ የተፈጸመውን ድርጊት በሰነድ በተደገፈ ሁኔታ ማቅረባቸውን የሚናገሩ አሉ። የለንደኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም እንዲሁ አይደለም እተጠቀሰው ብይን ላይ የደረሰው። ለጋሽ መንግሥታትና የእርዳታ ድርጅቶች ምኑን ነው የሚያስተባብሉት?

Landverpachtung an ausländische Investoren in Äthiopien

«ለጋሽ መንግሥታት ፤ በጋምቤላ የሠፈራ መርኀ ግብሩን በገንዘብ እንደማይደግፉ ነው የሚናገሩት። ይህ በቀጥታ ሲታይ ትክክል ነው። ነገር ግን የሚሰጡት ርዳታ፤ ለአካባቢያዊ አስተዳደሮች ይውላል፤ ለባለሥልጣናት ደመወዝ የሚሰጥም ከዚሁ ገንዘብ ነው። የሠፈራውን መርኀ ግብር ፣ ተግባራዊ ለሚያደርጉት ማለት ነው።

እኛን የ HRW ሰዎች የሚያሳስበን ፤ ለጋሾች፤ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ የሚፈጸመውን በደል ፣ በጥናት የተመሠረተውን ማለት ነው፤በቂ ምልክቶች ስለመኖራቸው መረጃ ቢቀርብላቸውም፤ ለመቆጣጠር ርምጃ አለመውሰዳቸው ነው። »

የኢትዮጵያን መንግሥት መምከርም ሆነ መገሰጽ ለምን፣ እንደተሣናቸው ሌሲ ሌፍኮቭ እንዲህ በማለት ሐሳባቸውን አጠቃለዋል።

«ብሪታንያና ሌሎች መንግሥታት፣ በግል፤ ጉዳዩ እጅግ እንደሚያሳስባቸው ይናገራሉ። ችግሩ ያለው መሻሻል አለማየታችን ላይ ነው። በለሆሳስ የሚደረግ ውይይት የሚከናወን ዲፕሎማሲያዊ ትግብርም ቢሆን፤አንዳች ውጤት አላሳየም። ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ፣ ተቃዋሚ የሚባሉትን ማዋካብ ማሳደድ የዞን 9 ጦማሪዎችን አፍሶ ማሠር ፤ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ፓርቲዎች አመራር አባላት፤ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአንድነት ለዴሞክራሲና አንድነት ፣ እንዲሁም ከዓረና ፣ ተይዘው ታሥረዋል። በዝግ በር የሚካሄድ ውይይት ፋይዳ ያለው ውጤት አላስገኘም።»

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic