የብሪታንያ ምርጫ ሒደት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የብሪታንያ ምርጫ ሒደት

በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት በሰወስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች መካካል የጎላ የመርሕ ልዩነት ባለመታየቱ የተመዘገበዉ ሁሉ ድምፁን መስጠቱ ብዙ አጠራጥሯል።

default

የሰወስቱ ፓርቲዎች መሪዎች

የብሪታንያ ሕዝብ የወደፊት እንደራሴዎቹን ለመምረጥ ዛሬ ድምፁን እየሰጠ ነዉ። ስድስት መቶ ሐምሳ መቀመጫዎች ላሉት ለሐገሪቱ ምክር ቤት አራት ሺሕ ያሕል እጩዎች ይወዳደራሉ። ምርጫዉን በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት ያሽንፋል ተብሎ የሚጠበቅ ፓርቲ ግን የለም። ድምፅ ለመስጠት ከአርባ አራት ሚሊዮን በላይ መራጭ ተመዝግቧል። ይሁንና በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት በሰወስቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች መካካል የጎላ የመርሕ ልዩነት ባለመታየቱ የተመዘገበዉ ሁሉ ድምፁን መስጠቱ ብዙ አጠራጥሯል።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ እንደታዘበዉ እስከ ቀትር ድረስ ድምፁን ለመስጠት የወጣዉ ሕዝብ ቁጥርም አነስተኛ ነዉ። ድልነሳን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።

ድልነሳ ጌታነህ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic