የብሪታንያ ህዝበ ውሳኔ | ዓለም | DW | 14.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የብሪታንያ ህዝበ ውሳኔ

ህዝበ ውሳኔውየሚካሄደው የብሪታንያ ጨቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ባለፈው ዓመት በብሪታኒያ ምርጫ በተካሄደበት ወቅት እርሳቸው እና ፓርቲያቸው ካሸነፉ ብሪታንያ የአውሮጳ ህብረት አባል ሆና ትዝለቅ ወይም አትዝለቅ የሚለውን ምርጫ ለህዝቡ አቀርባለሁ ባሉት መሠረት ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54

የብሪታንያ ህዝበ ውሳኔ

ብሪታንያ በአውሮጳ ህብረት አባልነት ትቀጥል ወይም አትቀጥል በሚል በቀረበለት ምርጫ ላይ የብሪታንያ ህዝብ በሚቀጥለው ሳምንት ሐሙስ ድምፅ ይሰጣል ። ይኽው ህዝበ ውሳኔ የሚካሄደው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ባለፈው ዓመት በብሪታኒያ ምርጫ በተካሄደበት ወቅት እርሳቸው እና ፓርቲያቸው ካሸነፉ ብሪታንያ የአውሮጳ ህብረት አባል ሆና ትዝለቅ ወይም አትዝለቅ የሚለውን ምርጫ ለህዝቡ አቀርባለሁ ባሉት መሠረት ነው ። ሰኔ 16፣ 2008 ዓም የሚካሄደው የዚህ ምርጫ ውጤት ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል ። የለንደኗ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ስለ ህዝበ ውሳኔው የሚሰጡ አስተያየቶችንና ብሪታንያ ከህብረቱ ብትወጣ ወይም ከህብረቱ ጋር ብትቆይ ታገኛለች የሚባለውን ጥቅምና ጉዳት በሚመለከት ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅታለች ።

ሃና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic