የብሪታንያው ልዑል ጋብቻ | ባህል | DW | 19.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የብሪታንያው ልዑል ጋብቻ

በበርካታ ብሪታንያውያን ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የልዑል ሃሪ እና የአሜሪካዊቷ ተዋናይት ሜጋን ማርክል የጋብቻ ስነ ስርዓት ዛሬ ተከናውኗል። ከመላው ዓለም የመጡ ከ120 ሺህ በላይ የንጉሳውያን ቤተሰብ አፍቃሪዎች ይህን ስነ ስርዓት በቦታው ተገኝተው የተከታተሉት ሲሆን ከ2 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ደግሞ በቀጥታ በቴሌቪዥን ተመልክቶታል ተብሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:14

የብሪታንያው ልዑል ጋብቻ

የዛሬዎቹ ሙሽሮች የልዑል ሃሪ እና አሜሪካዊቷ ሜጋን ማርክል ጋብቻቸውን የፈጸሙበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን በጎርጎሮሳውያኑ በ1528 ዓ.ም. የተመሰረተ ነው። ሰርጉ 2.7 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣ ሲሆን ወጪው በንግስት ኤልሳቤጥ የተፈሸነ ነው። የብሪታንያ መንግስት ለጸጥታ እና ጥበቃ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ አውጥቷል። ይህ የግብር ከፋይ ገንዘብ ለዚህ ዝግጅት ብቻ መውጣቱ ያበሳጫቸው ብሪታንያውያን 30 ሺህ ፊርማ በማሰባሰብ ተቃውሟቸውን ለሀገሪቱ የተወካዩች ምክር ቤት አስገብተዋል። 

እጅግ ዘመናዊ የንጉሳውያን ጋብቻ የታየበት የዛሬው የሰርግ ስነስርዓት ወግ አጥባቂውን ባህላዊውን የንጉሳውያን ቤተሰብ የሰርግ ስርዓት እምብዛም የተከተለ አልነበረም። 
ማንኛውም የፖለቲካ ባለስልጣን ከተመረጡ 600 እንግዶች መካከል አልተካተተም። በመልካም ስራቸው ማህበረሰሰቡን የሚያገለግሉ 1200 ሰዎች፣ የበጎ ሰናይ ድርጅቶች ሰርጉን እንዲታደሙ ከተመረጡት መካከል ናቸው።

የብሪታንያው ልዑል ሃሪ የጋብቻ ስነርዓትን አስመልክቶ የለንደኗ ወኪላችን ሀና ደምሴ ያጠናቀረችውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ሀና ደምሴ

ተስፋለም ወልደየስ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች