የብሉናይል ግጭትና የስደተኞች መበራከት | ኢትዮጵያ | DW | 28.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የብሉናይል ግጭትና የስደተኞች መበራከት

በሱዳን ብሉናይል ግዛት ከተቀሰቀሰዉ ግጭት ሸሽተዉ ወደጎረቤት ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ማሻቀቡን የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR አመለከተ።

default

ላለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ ወደሃያ አምስት ሺህ የተገመቱ ሱዳናዉያን ወደኢትዮጵያ መሰደዳቸዉ ሲገለፅ፤ ሌሎች አስር ሺዎችም ሊመጡ እንደሚችሉ ድርጅቱ ከወዲሁ አስታዉቋል። በተጠቀሰዉ አካባቢ የሚታየዉ ግጭት ጦርነት ወደሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ ይችላል የሚለዉ ስጋትም አይሏል። በኢትዮጵያ የUNHCR ህዝባዊ መረጃ ክፍል ኃላፊን በማነጋገር ሸዋዬ ለገሠ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic