የቤከር ኮሚሽን፣ ስለኢራቅ ያቀረበዉ የመፍትሄ ሃሳብ | የጋዜጦች አምድ | DW | 07.12.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

የቤከር ኮሚሽን፣ ስለኢራቅ ያቀረበዉ የመፍትሄ ሃሳብ

ኢራቅን ከዉጥረት ለማዉጣት የተሰየመዉ «ቤከር ኮሚሽን» በትናንትናዉ እለት በዋሽንግተን ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሪዝዳንት ጆርጅ ቡሽ የጥናቱን ይዘት አቅርቦአል

የቤከር ኮሚሽን እና ጆርጅ ቡሽ

የቤከር ኮሚሽን እና ጆርጅ ቡሽ

ከአሜሪካ ሁለቱ ታላላቅ ፓርቲዎች እና የዉጭ ፖሊሲ ኤክስፐርቶች የተዉጣጣዉ ይህ ቡድን እ.አ 2008 ዓ.ም ድረስ የአሜሪካ ጦር ሰራዊት ከኢራቅ እንዲወጣ፣ በተጨማሪ አሜሪካ በኢራቅ ጉዳይ ከኢራን እና ከሶሪያ ጋር እንድትወያይ ሃሳቡን ይሰጣል። ፕሪዝደንት ጆርጅ ቡሽ የአሜሪካን ወታደሮችን ከኢራቅ ለማስወጣትም ሆነ ከተጎራባች አገሮች ከኢራን እና ከሶርያ መደራደር ፍላጎት እንደሌላቸዉ መግለጻቸዉ የሚታወስ ነዉ። አሁን ትልቁ ጥያቄ የቤከር ኮሚሽን ስለኢራቅ የገመገመዉን እና መፍትሄ ያመጣል ያለዉን 79 ጽንሰ ሃሳብ የያዘዉን የመፍትሄ ሃሳብ ጆንጅ ቡሽ ገቢራዊ ያደሩጋታል? የሚለዉ ነዉ።
የቤከር ኮሚሽን ለኢራቅ መፍትሄ ይሆናል ያለዉን ሃሳብ፣ ፕሪዝደንት ጆርጅ ቡሽ መስማት እንጂ የመፈጸም ግዴታ እንደሌለባቸዉ ግልጽ ነዉ። ነገር ግን ትናንት ይህ የገምጋሚ እና የጥናት ቡድን ይፋ ያደረገዉ የመፍትሄ ሃሳብ ከተጠበቀዉ በላይ በጣም ግልጽ፣ እዉነታ ላይ የተመሰረተ እና፣ ነቃፊታ ሃሳቦችን የያዘ ሆኖ ነዉ የተገኘዉ። የየጥናት ቡድኑ በኢራቅ ጊዳይ፣ ጠንካራ በሆነ ግምገማ፣ በኢራቅ ያለዉ የርስ በርስ ጦርነትም ሆነ አስከፊ ጉዳይ አሰምቶአል። የአሜሪካኑ ፕሪዝደንትም ቡድኑ ያቀረበዉን ሪፖርት ባደመጡበት ወቅት፣ እንደ ሪት መራራ አይነቱን ክኒን የመዋጥ ያህል ሳይሰማቸዉ አልቀረም።
የኮሚሽኑ ባቀረበዉ የየመፍትሄ ሃሳብ፣ የአሜሪካ ወታደሮች ከኢራቅ መዉጣት እንዳለባቸዉ የሚገልጽ ሲሆን፣ ነገር ግን ጦሩ የሚወጣበት ቀን በግልጽ አለመነገሩ፣ ወይም ሃሳብ አለመሰጠቱ ቡሽን ደስ ሳያሰኛቸዉ አልቀረም። ያማለት ግን ከዚህ ቀደም ቡሽ እንዳሉት የአሜሪካን ወታደሮች ተልኮአቸዉን እስከ አላጠናቀቁ ድረስ አይወጡም የሚለዉን ሃሳብ ይጻረራል። እንዲህ አይነቱ ሃሳብ በአሜሪካ በህዳር ወር በተደረገዉ ምርጫ የዲሞክቶች አሸናፊነት ከተረጋገጠ በኳላ ግልጽ መሆኑ ይታወቃል።
እዚህ ላይ አንዱ በኢራቅ ለተከሰተዉ ጦርነት አባት የሆኑት እና የቀድሞዉ የመከላከያ ሚኒስቴር Donald Rumsfeld ስልጣን ከመልቀቃቸዉ በፊት በኢራቅ የሰፈሩትን የአሜሪካን ጦር ሰራዊት ቁጥር ለመቀነስ ግፊት አድርገዉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ። ቡሽ በዙርያቸዉ ያሉት የጦር ጀነራሎች እና መጭዉ የመከላከያ ሚኒስትራቸዉ፣ አሜሪካ በኢራቅ በአስነሳችዉ ጦርነት ሽንፈት እንደደረሰባት ቢነግሩዋቸዉም ቅሉ፣ በኢራቅ ስላላዉ ሁኔታ ጆርጅ ቡሽ አሁንም በመቀጠል ዉጤታማ እንደሆኑ ነዉ ከፍተኛ እምነት ያላቸዉ።
በፕሪዝደንት ቡሽ አባት ስልጣን ዘመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት ቤከር፣ ከቡድናቸዉ ጋር በመሆን በኢራቅ ያለዉ ሁኔታ በጣም ከባድ እና የተወሳሰበ ቢሆንም መፍትሄ ለማግኘት እንዲሁም ሊያስተካክሉት የሚችሉት ነገር እንዳለ ለማስተካከል እየሞከሩ መሆኑን ነዉ። ኢራቅ በዕርስ በርዕስ ጦርነት ዉስጥ ትገኛለች። የተለያየ እምነት በጎሳ ሰፊ ክፍተትን እያሳዩ የመጡት የሺኢት፣ የኩርድ፣ ሱኒት ጎሳዎች በመካከላቸዉ ያለዉን ዉጥረት ለመግታት የሚቻል አይመስልም። ነገርግን በየቦታዉ የሚነሳዉን ግጭት እና ዉጥረት በግድ መቀነስ እና መገታት ያለበት ጉዳይ ነዉ። በዚህም ምክንያት ፕሪዝደንት ቡሽ ከቤከር ኮሚሽን የቀረበላቸዉን የመፍትሄ ሃሳብ መቀበል ይኖርባቸዋል። ከኢራቅ አጎራባች አገር ከሆኑት ከሶርያ እና ከኢራን ጋር በጣም አስፈላጊ የተባለዉን የዲፕሎማሲ ዘመቻ መጀመር ይኖርባቸዋል። የኢራንም የአቶም መረሃግብር ርእስ ሆኖ ሊጠቀስም ይገባል። እንደ እዚህ ሃተታ ጻፊ አመለካከትም የቡሽ ከኢራቅ አጎራባቾች አገሮች ጋር ንግግር መድረክ ላይ መዉጣት አለማፈለጋቸዉ በእዉነቱ ፍሪቢስ እና ህጻንነት ነዉ! ከኢራን እና ከሶርያ ጋር ለሚደረገዉ የዲፕሎማሲ ዉይይት ምናልባትም የቀድሞዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጀምስ ቤከር ተገቢ ሰዉ ሊሆኑ ይችላሉ። ለዚህም ተጠቃሹ በመጀመርያዉ የፍርስ ባህረሰላጤ ጦርነት ቤከር፣ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሆነዉ በሚያገለግሉበት ወቅት ኢራቅን ከኩየት ለማስወጣት ሶርያ የአሜሪካ ወዳጅ ማድረግ መቻላቸዉ ነዉ ።
አሁንም ቢሆን ቤከር ለኢራቅ ሰላምን ለማንገስ አንዳችም መፍትሄ አላጋኙም ማለት አይቻልም። ምናልባትም የዚህ ጥናት ቡድን ያቀረበዉ ሃሳብ በኢራቅ ያለዉን ዉጥንቅጥ እና ችግር ቅነሳ ይረዳል የሚል ግምት አለ። ቢኖርም ግን ፍጹም መፍትሄ ይሆናል ማለቱ አጠራራጣሪ ነዉ። እዚህ ላይ ጀርመንም የቤከር የጥናት ቡድን ያቀረበዉን የመፍትሄ ሃሳብ መደገፍ ይኖርባታል። ያማለት የቡሽን አስተዳደር የሚደግፍ አይነት ሳይሆን ወይም የቡሽን አስተዳደር እድሜ የሚያራዝም አይነት ሳይሆን በኢራቅ አመታትንን ያስቆጠረዉን እና አስፈሪዉን ቃጠሎ ለማጥፋት የሚያስችል መሆን አለበት ።