1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤንዚን እጦት ፈተና የሆነባቸው የሀዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎች

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሐሙስ፣ ኅዳር 12 2017

ሀዋሳ በህጋዊ ማደያዎች ነዳጅ ማግኘት ሲበዛ አዳጋች ነው፡፡ በከተማው የነዳጅ አቅርቦት የለም ፡፡ በጥቁር ገበያው ላይ ግን አቅርቦቱ ተትረፍርፎ በየጎዳናው በፕላስቲክ ኮዳዎች ይቸበቸባል፡፡ ዋጋው ግን የሚቀመስ አይደለም ፡፡ መንግሥት በማደያዎች በሊትር 90 ብር እንዲሸጥ ብሎ ካስቀመጠው እዚህ በሁለትና በሦስት እጥፍ ይልቃል ፡፡

https://p.dw.com/p/4nGHM
በሃዋሳ ከተማ የቤንዚን እጦት
በሃዋሳ ከተማ የቤንዚን እጦት ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የቤንዚን እጦት ፈተና የሆነባቸው የሀዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎች

የቤንዚን እጦት ፈተና የሆነባቸው የሀዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎች

ያሬድ ሰለሞን እና ሰላሙ ሾዴ በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ ባጃጅ ተብለው የሚጠሩ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ኑሯቸውን ከሚገፉት መካከል ናቸው ፡፡ በከተማው እየተባባሰ በመጣው የቢንዚን እጦት ምክንያት ሥራ ለመሥራት መቸገራቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ያሬድ እና ሰላሙ “ የቢንዚን አለመኖር ህይወታችንን እያቃወሰብን ይገኛል ፡፡ አንዱን ቀን ሰርተን በቀጣዩ ቀን ቆመን ሥለምንውል የቀን ገቢያችን እንዲቀንስ አድርጎታል ፡፡ በዚህም የተነሳ  ቤተሰብ መመገብና ልጆች ማስተማር ችግር ሆኖብናል ብለዋል ፡፡

“ ቤንዚን የለም “

በሀዋሳ በህጋዊ ማደያዎች ነዳጅ ማግኘት ሲበዛ አዳጋች ነው ፡፡ በተለይ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በከተማው የነዳጅ አቅርቦት የለም ፡፡ በጥቁር ገበያው ላይ ግን አቅርቦቱ ተትረፍርፎ በየጎዳናው በፕላስቲክ ኮዳዎች ይቸበቸባል ፡፡ ዋጋው ግን የሚቀመስ አይደለም ፡፡ መንግሥት በማደያዎች በሊትር  90 ብር እንዲሸጥ ብሎ ካስቀመጠው እዚህ በሁለትና በሦስት እጥፍ ይልቃል   ፡፡  አሽከርካሪዎቹ ግን በማደያዎች ፍልገን ያጣነው ቤንዚን በጥቁር ገበያው እንዴት ተገኝ ሲሉ ይጠይቃሉ ፡፡  

በአገር አቀፍ ደረጃ የአቅርቦት እጥረት እንዳለ ብናውቅም የሀዋሳ ግን የባሰ መሆኑን የጠቀሱት የባጃጅ አሽከርካሪዎቹ ያሬድ እና ሰላሙ “ ማደያዎች በቀን ነዳጅ የለም በማለት በሌሊት ለጥቁር ገበያ ተቀባዮች  ሲሸጡ እናያልን ፡፡ ለሚመለከተው አካላት በተንቀሳቃሽ ሥልኮቻችን ጭምር ቀርጸን ጥቆማ ብናደርግም እርምጃ ሲወሰድ አላየንም ፡፡ መረጃ ቀርቦ አለአግባብ የሚጠቀሙ አካላትን ለምን ተጠያቂ ማድረግ እንዳልተቻለ  የክልል መንግሥት በደንብ ሊፈትሽ ይገባል “ ብለዋል ፡፡

የቤንዚን እጦት የሀዋሳ ከተማ
የቤንዚን እጦት የሀዋሳ ከተማ ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የጥቁር ገበያውን  ወደ መደበኛ የግብይት መሥመር

በከተማው የተከሰተው የቤንዚን አቅርቦት ቀውስ ያሳሰበውየሲዳማ ክልል በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ ግብረሃይል አዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል ፡፡ ግብረ ሃይሉ ዛሬ ከከተማው አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎች ፣ ከማደያ ባለቤቶችና ከህዝብ ትራንስፖርት ማህበራት ጋር ውይይት አካሄዷል ፡፡ በቢንዜን አቅርቦት ችግር የተነሳ ህዝቡ እየተማረረ መምጣቱን የጠቀሱት የግብረ ሃይሉ አባልና የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ  ጢሞጢዎስ “ ችግሩ የጸጥታ ሥጋት እስከመሆን ደርሷል “ ብሏል  ፡፡

“ መንግሥት የህዝቡን የኑሮ ጫና ለመቀነስ በከፍተኛ ድጎማ እያስገባ ያለው ቤንዚን  የጥቂቶች መክበሪያ እየሆነ ይገኛል “ ያሉት የቢሮው ሃላፊ “ በተለይ  በደላላ እና በመንግሥት ሙሰኞች እጅ የገባውን የግብይት ሥረዓት ከነገ ጀምሮ በአፋጣኝ ወደ መደበኛ የግብይት መሥመር የመመለስ ሥራ ይከናውናል ፡፡ ለዚህ ተባባሪ የማይሆኑ የማደያ ባለቤቶች ካሉ ግብረሃይሉ እንደማይታገስና  ህጋዊ ተጠያቂነትን የማስፈን ሥራም ተግባራዊ ይደረጋል  “ ብለዋል ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ