የቤናዚር ቡቶ፣ ህይወት ታሪክ | ዓለም | DW | 22.12.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቤናዚር ቡቶ፣ ህይወት ታሪክ

እኔ ላይ ያጠለለዉን አደጋ ወደጎን በመተዉ በአገሪ ላይ ያለዉን ችግር ለመቅረፍ እታገላለሁ ምክንያቱም የፓኪስታን ዉድ ልጆች ከአብራኬ እንደወጡ ልጆቼ የተከበሩ ናቸዉና ሲሉ በፓኪስታን ዲሞክራሲያዊ ስርአት መልሶ እንዲሰፍን ይታገሉ የነበሩት ቤናዚር ቡቶ ከመገደላቸዉ ሁለት ሳምንታት በፊት ለብዙሃን መገናኛ የሰጡት ቃል ነበር። የ 54 አመቷ ቀድሞዋ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትርና የተቃውሞው ወገን መሪ ቤናዚር ቡቶ በፓኪስታን ራዋልፒንዲ ከተማ ውስጥ ትናንት አን

default

ድ አጥፍቶ ጠፊ በተኮሰባቸዉ ጥይት ነበር አንገታቸዉ ላይ ክፉኛ ቆስለዉ ለእርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ያለፈዉ

ቤናዚር ቡቶ አገራቸዉ ፓኪስታንን በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለመጀመርያ ግዜ እንደ አ.አ 1988 እስከ 1990 ለሁለተኛ ግዜ 1993 እስከ 1996 አገልግለዋል። በእስልምና ሃይማኖት ተከታይ አገሮች ዘንድ ቡቶ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት አገራቸዉን የመሩ የመጀመሪያዋ ሴት ናቸዉ። የፊታችን ታህሳስ 29 በፓኪስታ ሊደረግ በታቀደዉ የምክር ቤት ምርጫ ለሶስተኛ ግዜ አገራቸዉን በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለመምራት ለዉድድር ቅድመ ዝግጅት ላይ ነበሩ። ለስምንት አመታት ያህል ማለትም እንደ አዉሮጻዉያኑ አቆጣጠር ከ1999 እስከ ያዝነዉ 2007 አ.ም ድረስ በተባበሩት አረብ ኢምራት፣ በዱባይ ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር በግዞት ኖረዉ ለብቻቸዉ ወደ አገራቸዉ በቅርቡ የተመለሱ ቢሆንም ለህይወት አስጊ የሆነ አደጋ እንደሚጣልባቸዉ ልቦናቸዉ በትክክል ያዉቀዉ እንደ ነበር ተገልጾአል። ዝርዝሩን ያድምጡ