የቤኒሻንጉል ግድያ፤ የህወሓት መሰረዘ፤ የረሃብ ሥጋት | የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት | DW | 22.01.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

የቤኒሻንጉል ግድያ፤ የህወሓት መሰረዘ፤ የረሃብ ሥጋት

ኦነግን ሳይሰርዝ የሞተውን ህወሓት መሰረዝ በህዝብ ላይ ማፌዝ ነው ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡት የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚ ናቸዉ። አሁን ህወሓት ሞቷል። ሀገር እያፈረሰ ያለውና ህጋዊ ሰውነት ያለው ኦነግ ነው። ኦነግ ከምርጫ ቦርድ ሳይሰረዝ ሌሎችን መስረዝ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ነው። ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:06

እረ ችግር ላይ ስላሉት ወገኖች እናስብ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ የቀጠለዉ ግድያ፤ የህወሓትን ህጋዊ ሰውነት መሰረዙ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የምግብ እጥረት አደጋ አንዣቦባቸዋል መባሉ ሰሞኑን በርካታ ኢትዮጵያዉያን በተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተወያዩባቸዉ ርዕሶች ናቸዉ። ለመሆኑ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚደጋገመውን እልቂት እና ግፍ የክልሉ አስተዳደር ማስቆሙ እንዴት ተሳነው? የፌዴራል መንግሥትስ ምን እያደረገ ነው?

ታደለ ሰለሞን የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ «በትክክል መተከልና ወለጋ የሰዉ ልጅ እንደእንስሳ የሚታረድበት በጅምላ ከሰዉ ክብር ወርደዉ የሚቀበሩበት የነፍሰ በላዎች ምድር ሆንዋል ሲሉ አስተያየታቸዉን አጋርተዋል። አቶ ገዛኸኝ ቶሌላራ በበኩላቸዉ  በሺዎች የተገደሉበት በትግራይስ ምነው አልተለቀሰላቸው? ምርጥ ኢትዮጵያዊ መስፈርታቸዉን አያሟሉም ይሁን? ሙሉአብርሃም ፍቅሬ ሌላዉ የፌስቡክ ተጠቃሚ  በአስተያየታቸዉ ኢትዮጵያ በርግጥ ሁሌም በአስጨናቂና አሳቃቂ በሚባሉ ወንጀለኞች የተሞላች እና ግን ድርጊቱን ፈፃሚዎችም ገድለው የማይቀሩባት በድህነት የምትማቅቅ ግን ምርጥ ህዝብ ያለባት ህገር ናት።

ይህንን ወንጀል ነው እርዳታችሁን ትሻለች ስንል ስንናገር በፍፁም አንሰማም ብላችሁ በእንግድነት የመጡባችሁን ኢትዮጵያውያንን የመኖርያ ወረቀት ከልክላችሁ ያለትምህርት ያለስራ ምግባረ ብልሹ አድርጋችሁት የሚንገላቱት ሲሉ ምዕራባዉያኑን ይተቻሉ።

የዓለም የምግብ ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ የግብረሰናይ ድርጅቶች ትግራይ ዉስጥ የረሃብ ስጋት አለ ሲሉ ዘግበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  በበኩሉ ጉዳዩን ሃሰት ሲል ያስተባበለዉ በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ላይ ነበር። ኮሚሽኑ በትግራይም ሆነ በቤኒሻንጉል አካባቢ ለተፈናቃዮች ሁሉ ምግብ እና ምግብ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን እየሰጠ መሆኑን አሳዉቋል። በትግራይ 485 ሺህ መፈናቀላቸዉን አሳዉቋል።  

አሚል አኪዎን የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛዎች ተጠቃሚ ዶክተር ዓቢይ ሰው የማያውቀውን እልቂት ለመከላከል ችላ ብሎታል። ሰው ግን እልቂቱን በዓይኑ ስላላየ ጉዳዩን ቀለል በማድረግ ችላ ብሎታል። እርዳታም ይሁን በየትኛውም ደረጃ ያሉ የውጭ ድርጅቶች ከእርዳታ ጋር አያይዘው ብጥብጥም የሚያስታጥቁ ናቸው። ዶክተር ዐቢይ ይሄን አውቀው ለየትኛውም የውጭ ድርጅቶች በርክፍት አላደረጉም ነበር ይሀው ህግ ማስከበሩ በቀላሉ ተቋጨ ይሄኔ ለውጭ ሀይሎች በር ቢከፍቱ ኖሮ አንደኛው ህወሃትን በመደገፍ ሌላኛው ዐቢይን በመደገፍ ኤርትራ ሱዳን ደቡብ ሱዳን ግብፅ ኬንያን በማጠቃለል አፍሪካን የጦር ቀጠና እና መሳሪያ ሽያጭን ያጣጡፉት ነበር።

አያሌዉ ታምራት በበኩላቸዉ እንደ መለስ የጠኔ እና የረሀብ ማብራሪያ ሲሰጥ ግን አልሰማሁም። ዙሮ ዙሮ ትግራይ ክልል ረሀብ አለ። የዛሬ ረሀብ መነሻው ደገግሞ ደጺ ትግራይ...በነበሩበት ወቅት ነው። መቸም ዛሬ አልተዘራም ተብሎ ዛሬ ረሀብ የለም፤ ይላሉ።

ሰላምታ በመስጠት አስተያየታቸዉን የሚጀምሩት ገብረሕይወት ወልደሰንበት ኢትዮጵያ ዉስጥ  ጤፍ 5000 ብር መግባቱ ረሃብ እንዳለ በቂ ማረጋገጫ ነው ይላሉ። የመንግስት ሰራተኛ የሆነውን እንኳ ብናይ አብዛኛው ደመወዙ 2000 ብር እና ከዛ በታች ሆኖ፤ ረሃብ የለም ብሎ በሰው ህይወት መቀለዱን ተረዱልኝ። እኔ የምኖረው መሀል ሀገር ነው። ቤተሰቤ ግን ትግራይ በመቀለ አቅራቢያ ነው። ቤት ንብረቴ በጦርነቱ ምክኒያት ወድሟል። ቤተሰቤም ተበትኖው ይገኛል። ሰርቼ ከማስተዳድርበት ደሞዝ ላይም ግማሹን፤ ለመከላከያ ሰራዊት መርጃ በሚል ይቆረጥብኛል። እናም እንደኔ ቤተሰብ አይነቶች በትግራይ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ እያለ፤ እንዲሁም ከትግራይ ክልል ውጭ በተለያዩ ክልሎች በርካታ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ እያሉ፤ በኢትዮጵያ ረሃብ የለም ማለቱ ምን ማለት እንደሆነ፤ ለዓለም መንግስታት አሳዉቁልን። እናም መንግስት ከህወሓት በምን ተሻለ ታዲያ? አመሰግናለው ብለዋል!

ከሃገሬ መንግስት ማንም አያቅም ከዶ/ር ዐብይ ዉጭ ወደውጭ እነደ መለስ በማንኪያ አቅምሶ በተሳቢ ለመዝረፍ አሁን በዐቢይ ጊዜ የለም የሞተው ሞቶ የቀረው ቀርቶ ኢትዮጵያ ዓለምን ትመራለች፤ያሉት ደግሞ ሞላ አቡኑ አካል የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ናቸዉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የ(ህወሓት)ን ህጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታዉቋል። ቡርዱ ይህን ይፋ እንዳደረገ ደሴ ዘ ታለም የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ አይ ምርጫ ቦርድ አሉ፤  አይ ምርጫ ቦርድ ህዝቡ እኮ ከእናተ በፊት ህወሓትን ከህጋዊ ፓርቲነት ሰርዟል።  ከዛም አልፎ አሸባሪ ብሎ ከፈረጃጀቸው እኮ ቆየ። ይህ ምን አዲስ ነገር ነውና ነዉ፤  እንደ አዲስ ዜና አጀንዳ የምትፈጥሩልን ሲሉ በጥያቄ አስተያየታቸዉን ደምድመዋል። የጊዮን ልጅ የተባሉ የፌስ ቡክ ተከታታይ አስተያየትም ደሴ ዘ ታለም ከሰጡት አስተያየት ብዙም አይለይም ከለውጡ ማግስት አብን ህወሓትን በአሸባሪነት ተፈርጆ ከህጋዊ ድርጅትነት ትሰረዝ በሚል ሲጮህ ያኔ ሰሚ አልነበረዉም። አሁን ጊዜው ደረሰና ህወሓት ተሰረዘች፤ ብለዋል።

Karte Äthiopien Metekel EN

ኦነግን ሳይሰርዝ የሞተውን ህወሓት መሰረዝ በህዝብ በህዝብ ላይ ማፌዝ ነው ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡት ደግሞ አሌክስ ዘ ጊዮን የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ተጠ ቃሚ ናቸዉ። አሁን ህወሓት ሞቷል። ሀገር እያፈረሰ ያለው እና ህጋዊ ሰውነት ያለው ኦነግ ነው። ኦነግ ከምርጫ ቦርድ ሳይሰረዝ ሌሎችን መስረዝ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ነው። ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።

አቶ መብራቱ ደሳለኝ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ያስቀመጡት አስተያየት ጥያቄም ይመስላል ለምርጫ ቦርድ፤ አሁንም በምርጫ ቦርድ ዘንድ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ሊያልፉ ሚችሉት ወደ 52 ፓርቲዎች ናቸው ተብሏል፡፡ አሁን  እውነት እነዚህ ፓርቲዎች ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን የሚወዱ ከሆነ እርስ በርስ በመቀራረብ ልዩነታቸውን አጥብበው ወደ ሁለት እና ሦስት አገራዊ ፓርቲነት ተቀይረው በመምጣት ለአገራችን እድገት እና እውነተኛ ዲሞክራሲ ያላቸውን ሃሳብ አቅርበው ያሳዩን!  ያበለዛ በብሔር በብሔሩ እየተሸጎጠ ሚመጣ ፓርቲ ለኢትዮጵያችን አንድነት እና ሰላም መርዝ ስለሆነ ብታፈርሱልን ደስታችን ነው!..እስኪ በህይወት ዘመናቹሁ ለህዝባቹሁ አንድ ጥሩ ነገር ስሩ! ሲሉ አሰያየታቸዉን ሰተዋል።

ሃኑካ ሺዳ የተባሉ በበኩላቸዉ ጥሩ ነው፤ ሲሉ አስተያየታቸዉን ጀምረዋል።  የፓርቲዎቹን ቁጥር ከ 113 ወደ 52 በዚህ ፍጥነት ማውረድ ከተቻለ ለሚቀጥለው ማለትም  (ከአምስት ዓመት በኋላ) ፓርቲዎቹ ከ 10 እንዳይበልጡ ማድረግ ይቻላል። የዓለምዘዉድ ቡዙነህ በበኩላቸዉ እረ በብሔር መሠባሠብ ይታገድ። ሁሉም ፓርቲዎች ዘመን ተሻጋሪ ትውልድ ቀራጭ ሥያሜ ይዘው ይምጡ ። ካልሆነ በብሔር የመሰባሰብ ፖለቲካ አይጠቅምም። በህግ ይታገድልን ይላሉ።

ተስፋ አዋሽ እንዲህ ይላሉ፤ 52 ፖርቲ ለአንድ ሀገር ድራማው ቀጥሏል። የአኛ ሀገር ፖለቲካ ፖርቲዎች ምርጫ ቦርድ ሳይሆን ንግድ ሚኒስቴር ነበር መመዝገብ የነበረባቸዉ።ህዝብ ለማገልገል ሳይሆን የህዝብን ሀብት ለመቀራመት የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች ናቸው።   

ሰለሞን ዳኘ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ምርጫ ቦርድ የህዉሀትን ሕጋዊ ሰዉነት ሲሰርዝ የሱን የያዘውን ባንዲራ ግን አልተሰረዘም ። መንፈሱን አንጂ መሰረዝ መንፈስ ተሸካሚውን አይደለም። እናም የህውሐት መንፈስ የሆነው የክልሉ ባንዲራ በሕግ ይታገድ። በተጨማሪም የክልል ባንዲራ በህዝብ ይሁንታ ቢመረጥ የፀዳ መንፈስ የፀዳን የክልል ተወካይ ፓርቲ ይፈጥራል።

አቡሽ ዘሪሁን ተረፈ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ እስካሁንም የፍቅሯ ነገር አልወጣላችሁ ብሎ እንጅ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከማገድ አልፎ እንደነ  አልሸባብ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የአሸባሪ ስብስብ በማለት በአሸባሪነት ትፈረጅ ነበር። ግን ምን ይሁን እሷ ያዘጋጀችዉን ያልተሻሻለ ገንጣይ ህገ-መንግስት እየተጠቀሙ ህጋዊ ሰዉነት ነፈግናት ቢባል ዉኃ ቅዳ ዉኃ መልስ ነዉ ነገሩ! ባይ ናቸዉ።  

ማያ የቲጂ ብለዉ ራሳቸዉን የሰየሙ የፌስ ቡክ ተከታታይ መሰረዛችሁ ካልቀረ ጨምሩና  አብይንም ሰርዙ ከዛም  እራሳችሁን ሰርዙ። አስመሳይ ሁላ ይላሉ በመቀጠል አስመሳይ ሁላ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ሳይሆን በጥያቄው ለመነገድ የተቋቋማችሁ ስለሆናችሁ ያቋቋማችሁን ህወሓትን ስትሰርዙ ሳትረሱ ራሳችሁንም መሰረዝ ነበረባችሁ። አስተያየታቸዉን ይቋጫሉ።

በ2013 ምርጫ ህወሓትን አለማየት ምን ያህል መታደል ነው! ያሉት የኔነህ መስፍን ትእግስት፤  እውነት እና እውቀት ኢትዮጵያን በሂደት ከሁሉ ክፉ ነገር ነፃ ያወጧታል ! ሲሉ ደምድመዋል። ነብዩ ዮሃንስ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ፤ የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል አደል የሚባለው ስንት የሚያዋልለን ነገር እያለ እንቶ ፎንቶ ትለቃለችሁ እረ ችግርላይ ስላሉት ወገኖች በየቀኑ ዘግቡ ተረት ተረት ሰለቸን ውይ!

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች