የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቃዮች ሰሚ ያጣ እሮሮ | ኢትዮጵያ | DW | 26.01.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቃዮች ሰሚ ያጣ እሮሮ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በንፁሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ እና ዘር ተኮር ጥቃት መንግሥት የክልሉን ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ካላደረገበት አይቆምም ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩና ቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቻቸው የተገደሉባቸው የአካባቢው ተወላጆች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:23

ነዋሪዎች፦ «ዘር ተኮር ጭፍጨፋው ስድስት ወር ሊሆነው ነው»

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እና ዘር ተኮር ጥቃት መንግሥት የክልሉ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ካላደረገ አይቆምም ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩና ቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቻቸው የተገደሉባቸው የመተከል ዞን ተወላጆች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የሃይማኖት መሪዎችና መገናኛ ብዙኃን እየደረሰ ያለውን ግፍ በቸልታ እየተመለከቱት ነው የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ እየተላኩ ያሉ የሰብአዊ ድጋፎችም አንድም በፀጥታ ሥጋት በፍጥነት እየደረሱ አይደለም፣ በሌላም በኩል ግብአቶቹን አዘጋጅቶ ለመጠቀም የመብራትና የውኃ እጥረት ፈተና ሆኗል ብለዋል። በመንግሥት ላይ ያጣነውን እምነት የሃይማኖት አባቶች እና የመገናኛ ብዙኃንም ነፍገውናል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ይኽ ሁሉ ግፍ እና ጭካኔ በመቶ ሺህዎችን ሲበላ የታሉ ሲሉም ምሬታቸውን ገልጠዋል። በቤንሻንጉል ክልል የብሔር ጥቃት ኼድ መለስ ቢልም በተደራጀ መልኩ እና ስውር ተልዕኮ እንዳለው በሚያሳይ መልኩ ተጠናክሮ  ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሲከናወንም ስድስት ወር ሊሆነው እንደሆነ ነዋሪዎች አቤት ብለዋል። 

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic