የቤት ኪራይ እና ኑሮ በወጣትነት | ባህል | DW | 03.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የቤት ኪራይ እና ኑሮ በወጣትነት

ከሚያገኙዋት ገንዘብ ከግማሽ በላይ ለቤት ኪራይ እየከፈሉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች ብዙ ናቸው። ቤት ተከራይቶ ኑሮ በአዲስ አበባ ምን ይመስላል?

አንድ ክፍል ቤት ናት ፤  መኝታውም ማብሰያውም እዛው ነው። መፀዳጃ ቤቱ ደግሞ በጋራ!  የቤቱ ኪራይ ግን  ሲጠሩት ያስደነግጣል።  አዲስ አበባ ውስጥ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ወጣቶች ስላነሳነው ጉዳይ ጠንቅቀው ያውቁታል። ለዛሬ ሁለት ወጣቶች በቤት ኪራይ እና ኑሮ ዙሪያ ተሞክሮዋቸውን እንዲያካፍሉን ጋብዘናል።

የሚከራይ ቤት ማግኘቱ ራሱ በጣም ከባድ ነው ትላለች፤ ነፃነት። ነፃነት እና ባለቤቷ ቤት ሲያፈላልጉ ብቻ ከአንድ ወር በላይ ፈጅቶባቸዋል። ደግነቱ በሁለት ደሞዝ ይኖራሉ እንጂ  የቤቱ ኪራይ ወጪ  ከነፃነት ገቢ ጋ ሲነፃፀር 80 በመቶ መሆኑን ገልፃልናለች።

ይህንኑ ጥያቄ ለወጣት አብይ አንስተንለታል ከደብረ ዘይት ከተማ ለቆ በአዲስ አበባ ሲኖር 10 አመቱ ነው። ከጓደኞች ጋ ተሰባስቦ መሞሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም አልተለመደም ይለናል። ተሰባስቦ በአንድ ላይ ቤት ተከራይቶ መኖር በትምህርት የመረዳዳት አጋጣሚዎችን ይፈጥራል። ብቸኝነትን ይቀንሳል። ቤት ውስጥ ሌሎች ሰዎችም አብረው ስለሚኖሩ ሁልጊዜ ቤቱን በንፅህና የመያዝ እና ሌሎች ጥሩ ጎኖችም አሉት።  የቤት ኪራይ ወጪ ራሱ አንዱ ምክንያት ነው።

ነፃነት እና አብይን እንደ አንድ ግለሰብ እና ተጠቃሚ መፍትሄ ይሆናል ብለው ስለሚያምኑትም አጫውተውናል።  ከድምፁ ዘገባ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic