የቤተ እስራኤላውያን የረሀብ አድማ | ኢትዮጵያ | DW | 20.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቤተ እስራኤላውያን የረሀብ አድማ

የረሀብ አድማ ከመቱ አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየኖሩ ወደ እስራኤል ለመሄድ በመጠባበቅ ላይ ከሚገኙ

default

ቤተ እስራኤላውያን መካከል ዛሬ የአንዲት የሀያ ሶሶት ዓመት ወጣት ህይወት አለፈ ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ እንደዘገበው ቤተ እስራኤላውያኑ የረሀብ አድማ የመቱበት ምክንያት ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያንን ሁኔታ ለመመልከት ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ የሄዱት አጣሪዎች የእነርሱ ጉዳይ ችላ ብለው በቀጥታ ወደ ጎንደር በማምራታቸው ነው ። ቤተ እስራኤላውያኑ እንደሚሉት እስራኤል የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጉዳያቸውን ለእስራኤል ፓርላማ ክኔሴት ያቀረቡ ሲሆን በዚሁ ጥያቄአቸው መነሻነትም ነው ለአጣሪዎቹ በጀት ተመድቦ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ የተደረገው ። ጌታቸው ተድላ የቤተ እስራኤላውያኑን አስተባባሪ አቶ ታምራት ፅዮንና ሌሎች ቤተ እስራኤላውያንን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።

ጌታቸው ተድላ ፣

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ