የቤተ እስራኤላዉያን ተቃዉሞ | ዓለም | DW | 31.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የቤተ እስራኤላዉያን ተቃዉሞ

ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ወጣት ዳንኤል ሰለሞን ለDW በስልክ እንደነገረን የእስራኤል ፖሊስና ባለሥልጣናት ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያንን ሲግድሉና ሲበድሉ የሰሞኑ የመጀመሪያዉ አይደለም።                           

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:10

ከዳንኤል ጋር የተደረገ ቃለ መጠየቅ

የእስራኤል ባለስልጣናትና ፖሊስ በኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉን ላይ ይፈፅሙታል የሚባለዉን የዘር ጭቆናና ግድያን በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን እስራኤላዉያን ትናንት ባደባባይ ሠልፍ ተቃዉሙ።ቴሌአቪ ዉስጥ አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ ከሁለት ሳምንት በፊት የሁዳ ቢያድጋ የተባለዉን ኢትዮጵያዊ እስራኤላዉ የአዕምሮ በሽተኛ ወጣት በጥይት ደብድቦ የገደለዉ ፖሊስ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቋልም።ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ወጣት ዳንኤል ሰለሞን ለDW በስልክ እንደነገረን የእስራኤል ፖሊስና ባለሥልጣናት ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያንን ሲግድሉና ሲበድሉ የሰሞኑ የመጀመሪያዉ አይደለም።በእስራኤል ምክር ቤት የሰብአዊ ሐብት ሎጂስቲክ አስተባባሪ አቶ ዮናታን ታከለ እንደሚሉት በኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያን ላይ የሚፈፀመዉ ግድያና በደል እንዲቆም ሕዝቡ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም እስካሁን ሁነኛ መፍትሔ አላገኘም።አቶ ዮናታን እንደሚሉት  በቅርቡ

የ24ት ዓመቱን  የዐዕምሮ ሕመምተኛ ወጣት የገደለዉ ፖሊስ ለፍርድ አለመቅረቡ ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያንን በጅጉ አስቆጥቷል።አቶ ዮናታንን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።ሟቹ ከዚሕ ቀደም የእስራኤል ጦር ሠራዊት ባልደረባ ነበር።የትናንትናዉን ሠልፍ ያስተባበሩት እንደገለጡት ሟቹ ከቤቱ ስለት ይዞ ሲወጣ  ፖሊስ እንዲረዳቸዉ ሥልክ ደዉለዉ የጠሩት ቤተሰቦቹ ናቸዉ።ለርዳታ የተጠራዉ ፖሊስ የዐዕምሮ ሕመምተኛዉን ወጣት በጥይት ደብድቦ ገደለዉ።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች