የቤተ እሥራኤላውያን የመብት ጥያቄ በኢየሩሳሌም | ዓለም | DW | 08.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቤተ እሥራኤላውያን የመብት ጥያቄ በኢየሩሳሌም

በእሥራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አይሁዳውያን መብታችን አልተከበረልንም በሚል ከሁለት ቀናት በፊት በኢየሩሳሌም በሚገኘው የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ደጃፍ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

የእሥራኤል መንግሥት ወደ ሀገሩ ከሚፈልሱት አይሁዳውያን ሁሉ ለኢትዮጵያውያኑ አይሁዳይውያን የተለየ አስተያየት በማድረግ ከሦስት አሠርተ ዓመታት በፊት እነዚሁ ወገኖች በቀላሉ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አንድ ሕግ አስተዋውቆ ነበር፤ ግን መንግሥት ከጥቂት ዓመታት በፊት በዚሁ ሕግ ላይ ያደረገው መጠነኛ ለውጥ ይህንኑ መብታቸውን እንደሚጋፋ ተቃውሞ የወጡት አይሁዳውያን ለሀይፋው ወኪላችን ግርማው አሻግሬ ገልጸውለታል።

ግርማው አሻግሬ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic