የቤተ-እሥራኤላዉያን የሥግድ በዓል | ባህል | DW | 05.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የቤተ-እሥራኤላዉያን የሥግድ በዓል

የኢትዮጳያ አይሁዶች ወይም ቤተ- እሥራኤላዉያን ባለፈዉ ሰሞን በየዓመቱ የሚያከብሩትን የሥግድ በዓል እያሩሳሌም ላይ በከፍተኛ ድምቀት አክብረዋል። የሥግድ በዓል በቤተ እሥራኤላዉያን ዘንድ እንዴት እና ለምን ይከበራል? በዕለቱ ዝግጅታችን ቤተ-እሥራኤላዉያን ስለሚያከብሩት የሥግድ በዓል ምንነት እንመለከታለን።

ከኢትዮጵያ ይዘነው የመጣነውን በዓል እዚህ እስራኤልም መጠበቅ አለብን፤ የስግድ በዓል የእምነት ጥንካሬና የአብሮነታችንም መግለጫ ቀን በመሆኑ በእስራኤልም አሁን ስንኖር ጠብቀነዉ እናከብረዋለን ሲሉ ባለፈዉ ሰምን እየሩሳሌም ላይ በድምቀት ስለተከበረዉ የስግድ በዓል የኢትዮጵያ አይሁዳዉያን አጠቃላይ ሊቀራባን ራቭ ዩሴፍ አዳነ ገልፀዉልናል። በቤተ- እስራኤላዉያን ዘንድ የሚከበረዉ የስግድ በዓል ከጥንታዊ የይሁዲ በዓልና ወግ የተወረሰ ከብዙ ሺ ዓመታት ጀምሮ በእኛ ተጠብቆ የቆየ ወደ እሰራኤል ከመጣንም በኋላም ለሕዝበ እስራኤል ይህን ይህን የጥንት በዓል መልሰን እያስተዋወቅን ነው ሲሉ ሊቀራባን ራቭ ዩሴፍ አዳነአጫዉተዉናል።
በእስራኤል በተለያየ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የስግድ በዓልን ለማክበር አዉቶቡስ በመከራየት ወደ እየሩሳሌም እንደሚመጡ የገለፁልን ራቭ ዩሴፍ አዳነ በዚህ እለት ብቻ ወደ ሰላሳ አርባ ሺህ ቤተእስራኤላዉያን የስግድ በዓልን ለማክበር ለመፀለይ ይመጣሉ።

Flash-Galerie Historische Nahostgespräche Stadt Jerusalem


ጎንደር አንቦበር በምትባል አካባቢ እንደተወለዱ የነገሩን በእስራኤል የኢትዮጵያ አይሁዳዉያን አጠቃላይ ሊቀራባን ራቭ ዩሴፍ አዳነ በ1961 ዓ,ም ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ጣልያን እንደወጡ ወደ ኢትዮጵያ አለመመለሳቸዉን ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ገና ይመጣሉ የሚባሉት የቤተ-እስራኤላዉያን ቁጥር ይሄን ያህል ነዉ ብሎ መናገር እደማይቻል የነገሩን ራቭ ዩሴፍ አዳነ ፤ እስራኤል ሃገር ከመጡት ቤተ-እስራኤላዉያን መካከል እኔ የመጀመርያዉ ነኝ ሲሉም አጫዉተዉናል።

ቤተ እስራኤላዉያን በየዓመቱ ጥቅምት መጨረሻ ላይ የሚያከብሩትን የስግድ በዓል በተመለከተ ያጠናቀርነዉ መሰናዶ የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። በእስራኤል የኢትዮጵያ አይሁዳዉያን አጠቃላይ ሊቀራባን ራቭ ዩሴፍ አዳነ ስለሰጡን ቃለ-ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም እናመሰግናለን።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic