የቤተክርስትያን ቀን አከባበር በጀርመን | ባህል | DW | 21.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የቤተክርስትያን ቀን አከባበር በጀርመን

በጀርመን በክርስትያኖች ህብረት የቤተክርስትያን ቀን በሚል ከአለም የተሰባሰቡ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ የተለያዩ ድርጅቶች የፖለቲካ ተጠሪዎች የባህል ተቋማት በአሉን ለአምስት ተከታታይ ቀናት አክብረዋል።

default

የቤተክርስትያን ቀን በሙኒክ ከተማ

በጀርመን የሚገኘዉ የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የበአሉ ተካፋይ ነበር በዛሪዉ ዝግጅታችን የምናነሳዉ አንዱ ርእስ ነዉ። የብሄር ብሄረሰቦች መኖርያ የሆነችዉ ኢትዮጽያ የተለያዩ ሃይማኖት ባህል እና አኗኗር ያላቸዉን ህዝቦች አቅፋ ትገኛለች። በተለይ የናይሎ ሳህራ ቋንቋ ዝርያን የሚናገሩ ሃያ ሁለት ያህል ብሄረሰቦች በደቡባዊ እና በምዕራባዊዉ የኢትዮጽያ ክፍል እንደሚገኙ ተገልጾአል። በዛሪዉ ዝግጅታችን በናይሎ ሳህራ ቋንቋ ተናጋሪ ብሄረሰቦች መካከል ጥቂቱን ባህላዊዉን የችግር መፍቻ ዘዴን እናያለን ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ

የቤተክርስትያን ቀን በተሰኘ ባለፈዉ ሳምንት በቫርያ ግዛት በሙኒክ ከተማ ለአምስት ቀናት በደማቅ ተከብሮአል። በተለይ የዘንድሮዉ የቤተክርስትያን ቀን ለየት የሚያደርግዉ የካቶሊካዉያን እና የወንጌላዊት ቤተክርስትያን በአንድ ላይ ማክበራቸዉ መሆኑ ተገልጾአል። ይህ አይነቱ የቤተክርስትያን ቀን እ.አ 2003 አ.ም በበርሊን የተከበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከሰባት አመት በኻላ በባቫርያ ግዛት በሙኒክ ከተማ ተከብሮአል። ኢትዮጽያዉያንም ተሳታፊ ነበሩ። በጀርመን የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሃላፊ ሊቃነካህናት ዶክተር መራዊ ተበጀ የዘንድሮዉ በል ለየት የሚያደርገዉ ይላሉ የወንጌላዊት የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በጥምር የሚያከብሩት በአል በመሆኑ እና በተለይ ከአለም ዙርያ የተሰባሰቡ የፖለቲካ ሰዎች የተለያዩ ሃይማኖትን የሚከተሉ ህዝቦች የተለያዩ ተቋማት በአንድ መድረክ በመሰባሰብ በተስፍ እንኑር በሚል መርሆ የዘንድሮዉን በአል ማክበራቸዉ ገልጸዋል። ያድምጡ!

የሱርማ ብሄረሰብ ባህላዊ የአመጽ እና ሰላም መጠበቅያ ወግ

ዛሪ በሁለተኝነት የያዝነዉ ርእሳችን በኢትዮጽያ ዙርያ ያቆየናል።

Äthiopien - Wahlen / Wartende vor Wahlkabine

የሙርሲ ብሄረሰቦች


የብሄር ብሄረሰቦች መኖርያ ኢትዮጽያችን የተለያዩ ባህል ወግ እና ሃይማኖት ያላቸዉን ህዝቦች አቅፍ ትገኛለች። በኢትዮጽያ የናይሎ ሰሃራ ቋንቋ ዝርያን ተናጋሪ ናቸዉ ተብለዉ የሚጠቀሱ ሃያ ሁለት ብሄረሰቦች እንዳሉ ምሁራን ይገልጻሉ በኢትዮጽያ የቋንቋ እና ባህል ተቋም ተጠሪ ዶክተር ባይለኘኝ ጣሰዉ በተለይ በጋምቤላ ዉስጥ ባሉት የኖር አኝዋክ ሱርማ ብሄረሰቦች ዙርያ ጥናት አካሂኦደዋል። በዛሪዉ ዝግጅታችን የናይሎ ሳህራ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆኑት ብሄረሰቦች መካከል የሱርማ ብሄረሰቦችን ባህላዊ የአመጽ እና ሰላም መጠበቅያ ወግ ድብድብ መሆኑን በኢትዮጽያ የቋንቋ እና ባህል ማዕከል ዶክተር ባይለየኝ ጣሰዉ ያጫዉቱናል ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

ተዛማጅ ዘገባዎች