“የቤተክርስቲያናት ክብርና አንድነት ይጠበቅ” በሚል በአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ ተደረገ | ኢትዮጵያ | DW | 15.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

“የቤተክርስቲያናት ክብርና አንድነት ይጠበቅ” በሚል በአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ ተደረገ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር የሚገኙ አድባራት ገዳማት በቤተክርስቲያኗ እና በአገልጋዮች ላይ የሚፈፀመው ግፍና በደል ይብቃ በሚል በተለያዩ ከተሞች ዛሬ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ

በጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻና በሌሎች ከተሞች ቤተክርስቲያኗን ከጥፋት ለመታደግ የሚያመለክቱ፣ አንድነቷን የሚያጠናክሩና ለአገር የዋለችውን አስተዋፅኦ የሚያሳዩ መፈክሮችን እያሰሙ ማርፈዳቸውን በየሰልፉ የተገኙ የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ በስልክ ገልፀዋል፡፡
በጎንደር ከተማ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የ44ቱም አቢያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችና እጅግ  ቁጥራቸው  የበዛ  ምእመናን ነጭ ልብሳቸውን ለብሰውና ቀሳውስትና ደቀመዛሙርት የዜማና የምስጋና መሳሪዎችን ይዘው ቅሬታቸውን ለመንግስት ማሰማታቸውን የሰልፉ አስተባባሪ ከሆኑት መካከል ቀሲስ ሰለሞን ዓለሙ ተናግረዋል፡፡
በደብረታቦር ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተገኙ አንድ የሰልፉ ተካፋይ እንዳሉት አንድ የሆነውን ሲኖዶስ እንደገና ለመከፋፈል የሚደረገውን ተንኮልና  አንዳንድ “የውጭ አጥኝ ነኝ” ባዮች ቤተክርስቲኒቱን ለመከፋፈል የሚያደርጉትን ሴራ ለማክሸፍ የተደረገ ሰልፍ መካሄዱን አብራርተዋል፡፡
የኮምቦልቻ ወረዳ ቤተክርስቲያናት አስተዳዳሪ መላከ ህይወት ቆስሞስ አባ ተክለማሪያም በበኩላቸው ከ1983 ዓ ም ወዲህ በቤተክርስቲያናትና በአገልጋዮቻቸው ላይ ግፍ እየበዛና እየከፋ መምጣቱን ጠቁመው ይህን ለመቃወም ምዕመናን ሰልፍ ወጥተው ድርጊቱ እንዲቆም መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡
14 አድባራትና ገዳማት የሚገኙባት ደሴ ከተማ ምዕመናንም የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ኢሳያስ ገላው እንደገለፁት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድሎ እየደረሰባት ነው፡፡

አለምነው መኮንን

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች