የቤርሉስኮኒ ስንብት እና በኢጣሊያ የመንግሥት ምስረታ ጥረት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 13.11.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የቤርሉስኮኒ ስንብት እና በኢጣሊያ የመንግሥት ምስረታ ጥረት

የኢጣሊያ ፕሬዚደንት ጆርጆ ናፖሊታኖ በአገሪቱ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ዘንድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ንግግር ጀመሩ።

default

ስልጣናቸዉን የለቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ

ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመታጨት የላቀ ዕድል ያላቸው ፖለቲከኛ የቀድሞው የአውሮፓ ሕብረት ኮሜሣር ማሪዮ ሞንቲ እንደሆኑ ተነግሯል። የኢጣሊያ የዜና ምንጮች እንደጠቆሙት የኤኮኖሚው ባለሙያ ሞንቲ ሥልጣን በለቀቁት በሢልቪዮ ቤርሉስኮኒ ፓርቲ ውስጥም ቀስ በቀስ ድጋፍ እያገኙ በመሄድ ላይ ናቸው። በሌላ በኩል የሽግግር መንግሥት ማቋቋሙ ካስቸገረ የም/ቤት ምርጫ እንደ አማራጭ መፍትሄ ሆኖ ተግባር ላይ ሊውል እንደሚችልም ለማወቅ ተችሏል። የ 75 ዓመቱ አንጋፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤርሉስኮኒ ትናንት የሮማ ፓርላማ በከባድ የመንግሥት ዕዳ በተወጠረችው አገር ላይ የጣለውን የቁጥባና የለውጥ መርህ ከተቀበለ በኋላ ሥልጣን መልቀቃቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

Italien / Rom / Berlusconi Rücktritt

ቤርሉስኮኒ በሙስናና በብልግና ድርጊቶች በአገሪቱ በየጊዜው ሲወቀሱና ሲወነጀሉ መቆየታቸው የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ዋና ከተማይቱ ሮማ ውስጥ ትናንት አያሌ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት በአከራካሪው ባለሥልጣን ስንብት የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን