የባቫሪያ (ባየር) ግዛት ልዑክ በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 16.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

  የባቫሪያ (ባየር) ግዛት ልዑክ በኢትዮጵያ

በግዛቲቱ ጠቅላይ ሚንስትር በዶክተር ማርኩስ ዘደር የተመራዉ የመልክተኞች ቡድን ትናንት ለኢትዮጵያዉያንና አዲስ አበባ ለሚኖሩ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶች የእራት ግብዣ አድርጓል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:13

የባቫሪያ ምሽት

Freistaat Bayern –(የባየር ወይም በእንግሊዝኛ ባቫርያ ነፃ አስተዳደር እንደማለት ነዉ-) ተብሎ የሚጠራዉ የደቡባዊ ጀርመን  ግዛት ባለስልጣናትና ባለሐብቶች ሠሞኑን ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነዉ።በግዛቲቱ ጠቅላይ ሚንስትር በዶክተር ማርኩስ ዘደር የተመራዉ የመልክተኞች ቡድን ትናንት ለኢትዮጵያዉያንና አዲስ አበባ ለሚኖሩ

የአፍሪቃ ዲፕሎማቶች የእራት ግብዣ አድርጓል።የባየር ምሽት በተባለዉ ድግስ ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ቫግነርና የጋባዦቹ መልዕክተኞቹ መሪ ዶክተር ማርኩስ ዘደር በየተራ ባሰሙት ንግግር መልዕክተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት በሐገሪቱ የሚደረገዉን ለዉጥ በቅርብ ለማየት ነዉ።ባየር በቆዳ ስፋት ከ16ቱ የጀርመን ክፍለ ግዛቶች የመጀመሪያዉን ደረጃ የያዘች ሐብታም ግዛት ናት።በሕዝብ ብዛት ደግሞ ከኖርድ ራይን ቬስት ፋለን ቀጥሎ ሁለተኛ ናት።

ጌታቸዉ ተድላ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች