የባራክ ኦባማ የበርሊን የስንብት ጉብኝት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 17.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የባራክ ኦባማ የበርሊን የስንብት ጉብኝት

የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለጉብኝት በርሊን የሚገኙትን የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ዛሬ ከቀትር በኋላ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለዋል። አሜሪካዊው ፕሬዚደንት ትናንት ምሽት ነበር ለሁለት ቀናት ጉብኝት በርሊን የገቡት።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:27
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:27 ደቂቃ

ባራክ ኦባማ በበርሊን

የፊታችን ጥር ወር ስልጣናቸውን በይፋ የሚያበቁት ኦባማ በስምንት ዓመቱ የስልጣን ዘመናቸው በርሊንን ሲጎበኙ ያሁኑ ስደስተኛ ጊዜአቸው ሲሆን ፣ይህ የመጨረሻቸውም ይሆናል።  ባራክ ኦባማ በዛሬው የመጀመሪያ የጉብኝት ቀን ከመራሒተ መንግሥቷ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በነገው ዕለት ከፈረንሳይ ፕሬዚደንት፣ ከኢጣልያ፣ ስጳኝ እና ከብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትሮች ጋር ተገናኝተው ንዑስ ጉባዔ እንደሚያካሂዱ ተሰምቶዋል።

ተሰናባቹ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጀርመንዋንን  መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልን ጥብቅ ወዳጅና በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ጠንካራ አጋር  ሲሉ አወድሰዋል። ኦባማ ትናንት ምሽት ጀርመን ከገቡ በኋላ ከመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል። ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኦባማ አንጌላ ሜርክልን አወድሰዋል። ኦባማ እንደሚሉት ሜርክል ከፍተኛ ተዓማኒነት ያላቸዉ መሪ ናቸዉ። በዚህ ምክንያትም ጀርመኖች ለመርያቸዉ ልዩ ክብር እንዲሰጡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ጠይቀዋል። ሁለቱ መሪዎች ከጋዜጣዊ መግለጫ በተጨማሪ በሁለቱ ሃገራት ግንኙነትና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል። በመጭዉ ጥር 12 ለተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በይፍ ስልጣናቸዉን የሚያስክቡት ባራክ ኦባማ ነገ በቀጣይ ወደ ፔሩ ያቀናሉ። 

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic