የባሕል መድረክ ኢትዮጽያ በአዉሮጻዉያን አይን | ባህል | DW | 03.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የባሕል መድረክ ኢትዮጽያ በአዉሮጻዉያን አይን

በኢትዮጽያን የሚያዉቁ በኢትዮጽያ የኖሩ የዉጭ አገር ዜጎች በተለይ ኢትዮጽያን ጥለዉ ሲወጡ ስለ አገሪቷ ዉበት በአገሪቷ ስላለዉ ብሄር ብሄረሰብ ስለ ህዝቧ ፍቅር፣ ስለወንዝ ተራራ እና ሜዳዉ በአጠቃላይ በአኢትዮጽያ ስላገኙት ተመክሮአቸዉ ተናግረዉ አይጨርሱም።

default

ሃንቡርግ ከተማ

ኢትዮጽያንም ለማስታወስ በኢትዮጽያ ያዩትን በፎቶ ካሜራ የቀረጹትን ለወዳጅ ለዘመድ በማሳየት ሲተርኩ፣ አልያም በመጽሃፍ መልክ ሲያሰፍሩ ከዝያም አልፎ ለአለም በአዲሱ ቴክኖሎጂ ዉጤት ኤንተርኔት ለህዝብ እያካፈሉ ፍቅራቸዉን ሲገልጹ ይታያል። የዛሪዉ መሰናዶአችን በኢትዮጽያ እትብቱ የተቀበረ ግሪካዊ በእንግድነት ይዘናል። እንግዳችን ፓኖስ ስክር ይባላሉ ከግሪካዊ አባታቸዉ እና ከጣልያናዊ እናታቸዉ አዲስ አበባ ላይ ነዉ የተወለዱት። ስለኢትዮጽያ በአገኙት አጋጣሚ ማዉሳታቸዉ እንደማይቀር ይናገራሉ። በኢትዮጽያ ሳሉ የጀርመን ትምህርት ቤት ገብተዉ ነዉ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ትምህርታቸዉን የተከታተሉት። በዚህም ትምህርት ቤት ታድያ አማረኛ መጻፍ ማንበብ ተምረዉ መነጋገር ብቻ ሳይሆን መጻፍ ማንበቡንም እንዲሁ አቃጥፈዉ ያዉቁታል። ኦሮምኛም ይሞካክራሉ። ከኢትዮጽያ ደግሞ በተለይ ጋንቤላን በፍቅር ያነስዋታል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ