የ«ባላገሩ ምርጥ» የድምፅ አሸናፊ ዳዊት ፅጌ | ባህል | DW | 12.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የ«ባላገሩ ምርጥ» የድምፅ አሸናፊ ዳዊት ፅጌ

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳ ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው የ«ባላገሩ ምርጥ» የሙዚቃ ዉድድር በድምፅ አሸናፊ የሆነው ዳዊት ፅጌ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:12
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:12 ደቂቃ

የ«ባላገሩ ምርጥ» የድምፅ አሸናፊ ዳዊት ፅጌ

በ 2008 ዓም በተጠናቀቀው የ«ባላገሩ ምርጥ» የዘፈን ውድድር በድምጽ አሸናፊ የሆነው ዳዊት ፅጌ ወደ ሙዚቃው ዓለም የገባሁት በ 2001 ዓም ነው ይላል። ከዛ በፊት ደግሞ በትምህርት ቤት ክበቦች እና አንዳንድ የሙዚቃ ዝግጅቶች ላይ ተካፍሏል። ዳዊት ፅጌ በተለያዩ የሥራ መስኮች የተሳተፈ ቢሆንም ዛሬ ትኩረት የምንሰጠው ከበርካታ ኢትዮጵያውያን ጋር ያስተዋወቀው የሙዚቃ ሥራ ላይ ነው።
የባላገሩ ምርጥ የ 300 000 ብር ተሸላሚ ዳዊት ፅጌ የሙዚቃ ችሎታውን ለማዳበር ልምምድ ከጀመረ ቆይቷል። በውድድሩ ጊዜ ደግሞ ትጋቱን ይበልጥ አጠናክሯል። በዚህ የሙዚቃ ውድድር ዳዊት ማሸነፉ ሕይወቱን በጥሩ መልኩ እንደቀየረም ገልጎልናል።ዳዊት በአሁኑ ሰዓት ከባላገሩ ጋር የጀመረው የሙዚቃ አልበም ላይ እየሠራ ይገኛል። ዳዊት ውድድሩ ዝና እና ገንዘብ ይዞለት ቢመጣም፤ ከአልኮል መጠጥ፣ ሲጋራ እና ጫት ከመሳሰሉት ርቆ እንደሚቆይ ይናገራል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በ2008 የተጠናቀቀው ባላገሩ አይደል ምርጥ የሙዚቃ ዉድድር የድምፅ አሸናፊ የሆነው ዳዊት ፅጌ ከዶይቸ ቬለ ጋር የነበረውን ቆይታ በድምፅ ያገኛሉ።


ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic