የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሱዳናውያን የፒኤችዲ ተማሪዎችን አስመረቀ | ኢትዮጵያ | DW | 23.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሱዳናውያን የፒኤችዲ ተማሪዎችን አስመረቀ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 8 ሱዳናውያንን ተቀብሎ በሶስተኛ ዲግሪ ማስመረቁን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። ተመራቂዎቹ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መማራቸው በሁለቱ አገራት ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚደርሰው አመልክተዋል፡፡ 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:29

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሱዳናውያን የፒኤችዲ ተማሪዎችን አስመረቀ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 8 ሱዳናውያንን ተቀብሎ በሶስተኛ ዲግሪ ማስመረቁን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፣ ተመራቂዎቹ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መማራቸው በሁለቱ አገራት ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚደርሰው አመልክተዋል፡፡ 
በባሕር ዳር ኒቨርሲቲ የሱዳንና የኢትዮጵያ ትምህርት ትብብር አስተባባሪ አቶ ሞገስ አብርሀ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ በሚባል ደረጃ 8 ሱዳንያውንን ተቀብሎ በሶስተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡ 
ዩኒቨርሲቲው ይህን ማድረጉ ምን ፋይዳ ስገኝለታል ተብለው የተጠየቁት አቶ ሞገስ ዩኒቨርሲቲው ዓለማቀፋዊነቱን ያሳደገዋል ነው ያሉት፡፡ 
ከዚህ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በሱዳን ካርቱም ሳተላይት መማሪያ ክፍሎችን በማዘጋጀት 90 ያህል ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት እየሰጠ ነው፡፡ 
በሁለቱ አገራት እየተደረገ ያለው ሁለትዮሽ የትምህርት ትብብር በሁለቱ አገራት ያለውን ግንኙነት ወደ ተሸለ ደረጃ እንደሚሳድገውም ተናግረዋል፡፡ 
ከተመራቂዎቹ መካከል ዶ/ር አህመድ መንሱር “ በሁለት አገሮች የምንኖር አንድ ህዝቦች ነን” ብሏል 
ሌላው ተመራቂ ዶ/ር ሀፊዝ አጅብ በበኩሉ “በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መማራችን በሁለቱ ህዝቦች ያለውን ወዳጅነትና አንድነት ያጠናክራል” ነው ያለው፡፡ 
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሱዳን በጠጨማሪ ከደቡብ ሱዳን፣ከሶማሌ ላንድ፣ከሶማሊያ፣ከሩዋንዳና ከቡሩንዲ ተማሪዎችን ተቀብሎ በተለያዩ ደረጃዎች እንደሚስተምር አቶ ሞገስ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ 

ዓለምነው መኮንን 
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

Audios and videos on the topic