የባህር ስደተኞች እና የአውሮጳ ህብረት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 05.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የባህር ስደተኞች እና የአውሮጳ ህብረት

ባለፈው የሳምንት መጨረሻ የኢጣልያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በሜድትሬንያን ባህር በበርካታ ትናንሽ ጀልባዎች ይጓዙ የነበሩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ማዳናቸዉ ተሰምቶዋል። የኢጣልያ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፣ በአሁኑ ጊዜ ባህሩ ፀጥ ባማለቱ እና ማዕበል ባለመኖሩ ነው ከሊቢያ ብዙ ጀልባዎች ስደተኞችን ወደ አውሮጳ ለማድረስ የተነሱት።

በሚቀጥሉትም ጊዚያት ወደ አውሮጳ ለመግባት የሚሞክሩት ስደተኞች ቁጥር እንደሚጨምር ነው ባለስልጣናት የሚገምቱት። ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ በሜድትሬንያን ባህር ስለተካሄደው ስደተኞችን የማዳን ተግባር እንዲያብራራልን ቀደም ሲል የሮሙን ወኪላችን ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic