የባህርዳር የዛሬ ውሎ | ኢትዮጵያ | DW | 24.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የባህርዳር የዛሬ ውሎ

በባህዳር መጠነኛ አረመረጋጋት መታየቱን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ካስታወቀ በኋላ በባህርዳር አለመረጋጋት መታየቱ ተሰምቷል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አቶ አበረ አዳሙ በሰጡት መግለጫ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ከትናንት በስተያ ተፈፀመ የተባለው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አቀነባባሪ የተባሉት ብርጋድየር ጀነራል አሳምነው ጽጌ መገደላቸው ከተሰማ በኋላ በባህዳር መጠነኛ አረመረጋጋት መታየቱ ተሰምቷል የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ካስታወቀ በኋላ በባህርዳር አለመረጋጋት መታየቱ ተሰምቷል። የአማራ ክልል የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ቀደም ሲል በሰጠው መግለጫ ግን ከተማዋ እየተረጋጋች ነው ብሎ ነበር። በሌላ በኩል በቅዳሜው ጥቃት ባህርዳር ውስጥ የሞቱት ባለሥልጣናት ቁጥር ዛሬ ወደ ሦስት ከፍ ብሏል። በወቅቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው  የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው የነበሩት የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ ማረፋቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን  ዛሬ ዘግበዋል። በቅዳሜው ጥቃት የክልሉ ፕሬዝዳንት ዶክተር አምባቸው መኮንን እና አማካሪያቸው አቶ አዘዘው ዋሴ ወዲያውኑ መሞታቸው ይታወቃል።  ከአማራ ክልል አመራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ  በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተገለፀ። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አቶ አበረ አዳሙ ማምሻዉን ለአማራ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ቅዳሜ ዕለት ከተገደሉት የክልሉ አመራሮች ጋር በተያያዘ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አመልክተዋል።ከጀነራሉ በተጨማሪም  ሌሎች አራት ተጠርጣሪዎች መያዛቸዉን አቶ አበረ አዳሙ ገልፀዋል። ከግድያዉ ጋር በተያያዘ «ዋነኛ ተጠርጣሪ» ተደርገዉ የነበሩት የክልሉ የፀጥታና የሰላም ግንባታ ጉዳዩች ቢሮ ሀላፊ ጀነራል አሳምነዉ ፅጌ መገደላቸዉ ከተገለፀ ከስዓት በኋላ በባህርዳር ከተማ አለመረጋጋት ሰፍኖ መታየቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች በዛሬዉ ዕለት በተረጋጋ ሁኔታ መደበኛ ስራቸዉን ሲያከናዉኑ የነበረ ቢሆንም የጀነራሉ መገደል ከተሰማ ወዲህ  አለመረጋጋት መታየቱ ተስተዉሎአል ተብሎአል።

ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

 


 
 

Audios and videos on the topic