የባህል ዝግጅት | ባህል | DW | 29.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የባህል ዝግጅት

በሰሜናዊ ጀርመን የወደብ ከተማ በሆነዉ በሃንቡርግ ከተማ የአዉሮጻ አገራትን ያሳተፈ የዳንስ ዉድድር መካሄዱ ሰሞኑን የጀርመን የባህል ድረ-ገጾች ካነስዋቸዉ ርዕሶች አንዱ ነበር። ይህ በአይነቱ ምናልባትም የመጀመርያ የተባለለት የዳንስ ዉድድር ከአለም አስቀያሚ ዳንስ በመደነስ አንደኛ የተባለን በማወዳደር ነዉ ሽልማትን ያበረከተዉ።

default

የዳንሱ ተወዳዳሪ

ዉድድሩን ያዘጋጀዉ ድርጅት ባለፉት አስራ አምስት እና ሃያ አመታት በተዜመ ግን በተሰለቸ መዚቃ አስቀያሚ ዉዝዋዜን በማድረግ ጥበብን ማሳየት ሲል ነበር ዉድድር እንደሚያደርግ ይፋ ያደረገዉ። የዉድድሩ ተካፋዮች በተለይ ከሉክስንበርግ ከስዊዘርላንድ እና ከጀርመን የተሰባሰቡ ሲሆን የዳንስ ዉድድሩ ተካፋዮች አይን በማይገባ ወይም በማይጥም አይነት አለባበስ እና ለጆሮ በተሰለቸ ሙዚቃ ዉዝዋዜን በማሳየት አዲስ ጥበብን ማምጣት ነበር። በዉድድሩ የአሸናፊች አሸናፊ በመሆን ከዚሁ ከጀርመን ከሃንቡርግ ከተማ መቶ ሃምሳ ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘዉ ሽታይን ፊልድ ከምትባለል አንዲት ገጠር የመጡ አራት ወጣቶች የዉድድሩ አሸናፊ በመሆን ከአለም አስቀያሚዉን ዳንስ በመደነስ አንደኛ በመሆን ተመርጠዋል። አራቱ ወጣቶች ዲሴንቲነር የዳንስ ቡድን ብለዉ ቡድናቸዉን የሰየሙ ሲሆን በተሰለቸ ሙዚቃ እና በማይጥም አይነት አለባበስ የማያምር ዉዝዋዜን በማሳየት ከአለም አንደኛ በመሆን ተመዝግበዋል። ዋናዉ ግን ይላል የዉድድሩ አዘጋጅ ይህን አስቀያሚ ዳንስ ለማሳየት የተጠቀሙበት ጥበብ ተጠቃሽ ነዉ። ታድያ ባለፈዉ ቅዳሜ በሃንቡርግ የተካሄደዉ የዳንስ ዉድድር ሰሞኑን የጀርመን የበህል ድረ-ገጾች ካተኮሩባቸዉ ርእሶች መካከል አንዱ ነበር።

Ugly Dance Worldcup Hamburg Flash-Galerie

የዳንስ ዉድድሩ አሸናፊዎች

በአለም የስፖርት አፍቃሪ ዘንድ ታዋቂ የነበረዉ ባለ ስድስት እግሩ ዝልግልግ አሳ መሞቱ ሰሞኑን የጀርመን የብዙሃን መገናኛዎች እና የኢንተርኔት ድረ-ገጾችን ቀልብ የሳበ ጉዳይ ነዉ። እዚህ በጀርመን በቦርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት ኦበርንሃዉዝንን ከተማ ዉስጥ ባለ አኳሪዮም ማለት በዉሃ ዉስጥ የሚኖሩ የተለያዩ እንስሳት እንዲራቡም ሆነ ሰዉ እንዲጎበኛቸዉ በሚኖሩበት ሰዉ ሰራሽ ግዙፍ ገንዳ ዉስጥ ይኖር የነበረ ዝልግ አሳ ፓዉል የሚል መጠርያም ነበረዉ። ይህ ሶስት አመት ግድም እድሜ እንዳለዉ የተነገረለት ባለ ስድስት እግር ዝልግልግ አሳ ታዋቂነትን ያገኘዉ በደቡብ አፍሪቃ በተካሄደዉ የአለም የእግር ኳስ ግጥምያ ዉድድር ላይ ነበር። ጀርመናዉያን ፓዉል የሚል መጠርያ የተሰጠዉ ዝልግልግ አሳ ጀርመን የእግር ኳስ ቡድን ከስፔን ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር የግማሽ ፍጻሜ ዉድድር ሊያደርግ ሲዘጋጅ ስፔን ታሸንፋለች የሚል ምልክት አሳይቶአል ተብሎ እዉነትም ስፔን በማሸነፍዋ ነበር። በጀርመን እዉቅ የነበረዉ ይህ ዝልግልግ አሳ በሚኖርበት የመስታወት ገንዳ ዉስጥ የእግር ኳስ አፍቃሪ የሆነዉ ጀርመናዉያን በመስታወቱ ላይ በአንድ በኩል የጀርመንን በሌላ በኩል የስፔንን ባንዲራ ለጥፈዉ በሁለቱም በኩል ዝልግልጉ አሳ ፓዉል የሚበላዉን ምግብ በትነዉ፣ ባለ ስድስት እግሩ አሳ በስድስት እግሮቹ ቀዝፎ ምግብ በመጀመርያ ለመብላት አፉን በከፈተበት ወገን ያለዉ ባንዲራ አሸናፊ አገር ነዉ በመባል የአግር ኳስ ግጥምያዉ ሰሞን ፓዉል ታዋቂ ተንባይ ሆኖ ሰንብቶ ነበር። በዚህም የተለያዩ ቡድኖች ሲጫወቱ ስምንት ግዜ ትንበያዉ ትክክል መምጣቱ የአለም የእግር ኳስ አፍቃሪ በተለይ በተለይ ደግሞ ምዕራባዉያኑ ያምኑበትም ነበር። በደቡብ አፍሪካዉ የእግር ኳስ ዉድድር በጀርመን እና በስፔን መካከል በተደረገ የግማሽ ፍጻሜ ዉድድር ፓዉል እንደተነበየዉ እስፔን በማሸነፍዋ በርካታ የጀርመን ደጋፊዎች በርግጥም ለዝልግልጉ አሳ ፓዉል ሞትን ከዝያም አልፎ ከጥሩ ድንች ጥብስ ጋር ጠብሰዉ ሊበሉት ተመኝተዉ ነበር። ከእግር ኳሱ ዉድድር በኋላ ይህን ሁኔታ የሰሙ የእስፔኑ ፕሪዝደንት ጆሴ ሉዊስ ሳፓቴሮ ዝልግልጉ አሳ ፓዉል ህይወት ጉዳይ ሃሳብ እንደያዛቸዉ መናገራቸዉን መግለጻቸዉ ዘግቦአል። ጀርመናዉያኑ በንዴት ጠብሰዉ እንዳይበሉት ብለዉ በማሰብ ማለት ነዉ። የስፔን ኢንዱስትሪ ሚንስትር እና የአካባቢ ጉዳይ ሚኒስትርም እንዲሁ ስለ ዝልግልጉ አሳ ፓዉል ጉዳይ በሃሳብ መጠመዳቸዉን መግለጻቸዉ የአንድ ሰሞን መዝናኛ ዜና ሆኖ ሰንብቶአል። በሌላ በኩል ፓዉል ለስፔን ይህን ጥሩ ትንበያ ካስቀመጠ በኳላ በርካታ የእንስሳት ጉዳይ ተቆርቋሪዎች አሳዉ ከተቀመጠበት ሰዉ ሰራሽ ኩሪ ወቶ ወደ ትዉልድ መንደሩ ወደ አትላቲክ ባህር በነጻ ይለቀቅ ማለታቸዉም ተዘግቦአል። በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ ለማክሰኞ አጥብያ የሞተዉ አሳ ያላምንም እክል በድሜዉ እንደሞተ የብዙሃን መገናኛዎች ማክሰኞ ማለዳ ሲዘግቡ አርፍደዋል። የስፔን የእግር ኳስ አፍቃሪ ግን በፓዉል ድንገተኛ ሞት መደናገጣቸዉን በርካታ ጋዜጦች መዘገባቸዉ ተገልጾአል። እንደዉም አንዱ ጋዜጣ የአሳዉን ጥሩነት በመግለጽ ለምን ጥሩ የሆኑ ነገሮች ይችን አለማችንን በቶሎ ይለቃሉ ሲል መጻፉ በርካታ አድማጮችን እና አንባቢዎችን ፈገግ ሳያሰኝ አልቀረም። ይህን አይነቱን አሳ መብላት ልማድ በሆነበት በዚህ በአዉሮጻም በተለይ እስፔናዉያን የፓዉል አፍቃሪዎች እንዲህ አይነቱን አሳ ስንበላ ፓዉልን ማሰባችን አይቀሪ ነዉ ሲሉ መግለጻቸዉም ተነግሮአል። በሌላ በኩል በጀርመን ፓዉልን ይኖርበት በነበረዉ በኦበርንሃዉዝን ግዙፍ ገንዳ የሚኖር ሌላ ፓዉልን የሚተካ አሳ ለማምጣት እና ጀርመናዉያን እ 2012 አ.ም የአዉሮጻ የእግር ኳስ ዋንጫ ዉድድር ላይ እንዲተነብይ እንደሚያደርጉ እና ለፓዉል እዝያዉ ፓዉል ይኖርበት በነበረዉ የባህር እንስሳት እንዲራቡ፣ በሚኖሩ፣ በሚደረግበት ግዙፍ ገንዳ አካባቢ ማስታወሻ ሃዉልት እንደሚሰራለት መገለጹ ሲያዝናና የነበረ እና በተለያዩ በባህል እና በስፖርት ድረ-ገጾች ያተኩሩበት ርዕስ ነበር።
ሊስትሮ ፕሮጀክት

Flash-Galerie Krake Paul Oktopus Fußball

የእግር ኳስ አሸናፊ ተንባዪ ዝልግልግ አሳ


በያዝነዉ ሳምንት በበርሊን የሚገኝ ሊስትሮ የተባለ ፕሮጀክት በኢትዮጽያ ወጣቶች በሊስትሮ ስራ ኑሮአቸዋን እንዲት እንደሚያሸንፉ የሚያሳይ ኢግዚቢሽ ተከፍቶአል። በስነ-ስርአቱ ላይ የጀርመኑ ርዕሰ ብሄር ክርስትያን ዎልፍ ተገኝተዉ ኢግዚቢሽኑን ጎብኝተዋል። በልጅነት ያላቸዉንም ተመክሮ አካፍለዋል። በስነ-ስርአቱ ላይ በበርሊን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮያዉያን እና በርካታ ጀርመናዉያን ተገኝተዉ ነበር። በኢትዮጽያ በሊስትሮ ስራ የሚተዳደሩ ህጻናት እና ወጣቶችን ተግባር የሚያንጸባርቅ እዝያዉ በኢትዮጽያ በወጣትቶቹ እጅ የተሰራ ሶስት ሽህ አምስት መቶ ያህል የሊስትሮ ሳጥን ለእይታ ቀርቦአል። ከሊስትሮዎቹ ለጀርመናዉያኑ የተጻፈም ደብዳቤ የኢግዚቢሽኑ አንድ አካልም ነበር። የሊስትሮ ፕሮጀክት መስራች ዳዊት ሳንቆን አንድ ሳምንት ስለሚዘልቀዉ ኢግዚቢሽን አነጋግረናል! ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ